Ethiopian Electric Power

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ብልሽቱን ለማስተካከል አራት ቀን ይፈጃል

ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 22, 2020)፦ በአማራና በትግራይ ክልሎች የሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋረጠባቸው ተገለጸ።

የሁለቱ ክልሎች በተወሰኑ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የተቋረጠባቸው በአላማጣ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመር ላይ በደረሰ ብልሽት እንደኾነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኢቢሲ ገልጿል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋረጠባቸው ከተሞች መካከል ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ማይጨውና አላማጣ ይገኙበታል ተብሏል። ብልሽቱን ለማስተካከል አራት ቀን ይፈጃልም ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ