NAMN and TPLF

አብን እና ሕወሓት

ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል የተካለሉት እንደ ወልቃይት፣ ሑመራ፣ ራያ፣ ጠለምት እና የመሳሰሉት አካባቢዎች ላይ ነው እግዱን የሚጠይቀው

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 23, 2020)፦ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል የተከለሉ ናቸው ባላቸው አካባቢዎች ምርጫ እንዳይካሔድ የእግድ ጥያቄ ሊያቀርብ ስለመኾኑ ተገለጸ።

የአብን አንድ ከፍተኛ አመራር ለኢትዮ ኤፍ.ኤም ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም. እንዳስታወቁት፤ ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል የተካለሉት እንደ ወልቃይት፣ ሑመራ፣ ራያ፣ ጠለምት እና የመሳሰሉት አካባቢዎች የትግራይ ክልል ምርጫ እንዳያካሒድ የእግድ ጥያቄ የሚያቀርቡ መኾኑን ነው።

አብን በእነዚህ ያለአግባብ ወደ ትግራይ ክልል በተካለሉት አካባቢዎች አብን በምርጫ የሚወዳደር መኾኑን በመግለጽ፤ በማኒፌስቶው ያስቀመጠ በመኾኑ፤ የትግራይ ክልል ደግሞ አካሒደዋለሁ ማለቱን በመቃወም፤ በእነዚህ አካባቢዎች ምርጫ እንዳይካሔድ ለማድረግ የእግድ ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መኾኑም ተጠቅሷል።

በመሠረታዊነት የትግራይ ክልል የምርጫ እንቅስቃሴ ሕገ መንገሥታዊ እንዳልኾነ ቢታወቅም፤ በአብን በኩል በተለይ ሊወዳደርባቸው የነበሩት ቦታዎች ላይ ምርጫው እንዳይደረግ እገዳ እንዲጣል ጥያቄያቸውን እንደሚያቀርቡም እኒሁ የአብን ከፍተኛ አመራር ከሰጡት ቃለ ምልልስ ለመገንዘብ ተችሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ