Ethiopia, Djibouti and Rwanda

ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳና ጅቡቲ

በሁለቱ አገራት ጥቂት ያልኾኑ በወንጀል የሚፈለጉ ኢትዮጵያውያኖች እንዳሉ ይነገራል

ኢዛ (ዓርብ ሰኔ ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 26, 2020)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ ከጅቡቲና ከሩዋንዳ ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችላቸው ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ መንግሥት፣ በሩዋንዳ ሪፐብሊክ እና በጅቡቲ መንግሥታት መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር ስምምነት በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት ረቂቅ አዋጆችን ተመልክቶ ያጸደቀው ትናንት ሐሙስ ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው።

 

ቁጥራቸው ጥቂት ያልኾኑ በወንጀል የሚፈለጉ ኢትዮጵያውያን በሩዋንዳ እና በጀቡቲ እንደሚገኙ ይነገራል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ