የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በዝግ ስብሰባ ተቀምጠዋል
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ
ወሳኝ የተባሉ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሏል
ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 10, 2020)፦ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ለሁለት ቀናት ያካሔደው ዝግ ስብሰባ መጠናቀቅ ማግሥት የአማራ ብልጽግና ፓርቲም በዝግ ስብሰባ እየተወያየ ይገኛል።
ነገ ማምሻውን ይጠናቀቃል በተባለው የአማራ ብልጽግና ዝግ ስብሰባውን እያካሔደ ያለው በባሕር ዳር ከተማ ሲሆን፤ በዚህ ውይይት የክልሉና የዞን ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮችን ያሳተፈ ነው።
የውይይቱ በዋናነት በአገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ግምገማ የሚደረግ ሲሆን፤ ከለውጡ በኋላ ያለውን ሒደት ይገመግማል ተብሏል። ስብሰባው ወሳኝ የተባሉ ጉዳዮች ላይም በመነጋገር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። (ኢዛ)



