Lidetu Ayalew

አቶ ልደቱ አያሌው

ፖሊስ ያሰርኳቸው በአደራ ነው ብሏል

ኢዛ (ረቡዕ መስከረም ፲፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 23, 2020)፦ ትናንት በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈቀደላቸው አቶ ልደቱ አያሌው እስካሁን አለመለቀቃቸው ተገለጸ።

የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ እንደገለጹት በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሠረት ለዋስትና የተጠየቀው 100 ሺህ ብር ተከፍሎ የማስፈቻ ትእዛዙን ጭምር ብንይዝም፤ ፖሊስ ሊለቃቸው አልቻለም ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በተለይ ለጀርመን ድምፅ ራዲዮ እንደገለጹት፤ አቶ ልደቱ የታሰሩትበት ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች፤ “አቶ ልደቱ እዚህ ያሉት በአደራ ነውና፤ መልቀቅ አንችልም” ማለታቸውን አስረድተዋል።

አቶ ልደቱን መልቀቅም ማሰርም ሥልጣን ያለው አካል ሌላ ነው በመባሉ፤ ሥልጣን ያለውን አካል አዳማ ነው ተብለው ወደዚያው ካቀኑ በኋላ እንደገና ወደ ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ስለመመለሳቸውም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ