የአቶ ዳውድ መግለጫ በጸጥታ ኃይሎች መቋረጡ ተነገረ

አቶ ዳውድ ኢብሳ
በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የለም
ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ በቅርቡ በኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከኦነግ ሊቀመንበርነታቸው ተነስተዋል የተባሉት አቶ ዳውድ ኢብሳ፤ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በመኖሪያ ቤታቸው ሊሰጡ የነበረው መግለጫ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች መቋረጡ ተነገረ።
የአቶ ዳውድ መግለጫ እንዲቋረጥ የተደረገበት ምክንያት ያልተገለጸ ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የለም። (ኢዛ)