The new forged 100 birr notes

ሐሰተኛ የአዲሱ ባለ 100 ብር ኖሮች

በሐሰተኛ መንገድ የተዘጋጁ 200 ሺህ የብር ኖቶችና 174 ሺህ 350 የነባሩ ብር ኖቶች ተይዘዋል
በሐሰት የተዘጋጀው ዶላር 14,800 ነው

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 30, 2020)፦ የፌዴራል ፖሊስ የአዲሱንና የነባሩን (የአሮጌውን) ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች እና በተመሳሳይ መንገድ ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላሮችን መያዙን አስታወቀ።

በመረጃው መሠረት ሐሰተኛ የብር ኖቶቹ እና ሐሰተኛ የዶላር ኖቶቹ በአጠቃላይ ወደ 400 ሺህ ብር የሚጠጋ መጠን ያላቸው ናቸው ተብሏል።

174,350 ሐሰተኛ የነባሩ ብር ኖቶች ከሁለት ተጠርጣሪዎች የተያዙ ሲሆን፤ እነዚህ ሐሰተኛ የብር ኖቶች የባለ 100 እና የባለ 50 ብር ኖቶች ናቸው።

ሐሰተኛ የአዲሱ ብር ኖቶች የተያዙት ደግሞ ከአንድ ግለሰብ ላይ ሲሆን፤ በባለ 200 እና በባለ አንድ መቶ ብር የተዘጋጁት እነዚህ የአዲሱ ሐሰተኛ የብር ኖቶች 200 ሺህ ሐሰተኛ ብር ነው።

በሐሰተኛ መንገድ ተዘጋጅተው ከተያዙት የአዲሱና የነባሩ ብር ኖቶች ሌላ፤ በሐሰተኛ መንገድ የተዘጋጁ 14,800 ሐሰተኛ ባለ መቶና ሃምሳ የአሜሪካ ዶላር መያዙንም ይኸው መረጃ ያመለክታል። ይህንን ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠሩት ላይ የክስ መዝገቦች ተከፍተው ጉዳዩ እየተጥጣራ ስለመኾኑ ተገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ