Chairperson of the African Union Commission Moussa Faki

የአፍሪካ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማት

ሜ/ጄኔራል ገብረእግዚአብሔር መብራቱ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ብርጋዲየር ጄኔራል ኃይሉ ጎንፋ ተተኩ

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 13, 2020)፦ የመከላከያ ሚኒስቴር የአፍሪካ ሕብረት የጸጥታ ኃላፊ በመኾን ሲያገለግሉ የቆዩት ሜጀር ጄኔራል ገብረእግዚአቤር መብራቱ መለስ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱና በምትካቸው አዲስ ኃላፊ መሾሙን ባስታወቀው መሠረት፤ ሕብረቱ ኃላፊውን አሰናበተ።

መከላከያ ሚኒስቴር ለአፍሪካ ሕብረት በላከው ደብዳቤ የአፍሪካ ሕብረትን የጸጥታ ኃላፊ በመኾን ሲሠሩ የነበሩትን ሜጀር ጄኔራል ገብረእግዚአብሔርን ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን እና በምትካቸው ብርጋዲየር ጄኔራል ኃይሉ ጎንፋ መመደባቸውን ለሕብረቱ አስታውቆ ነበር።

ሜጀር ጄኔራሉ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ከወቅታዊው አገራዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ስለመኾኑ ሚኒስቴሩ ለአፍሪካ ሕብረት በላከው ደብዳቤ ጠቅሶ እንደነበር ታውቋል።

በዚሁ መሠረት ደብዳቤው በተላከ በ72 ሰዓታት ውስጥ የቀድሞው ኃላፊ ለአዲሱ ኃላፊ በ72 ሰዓታት ውስጥ እንዲያስረክብም ሚኒስቴሩ ባሰሰበው መሠረት፤ ሕብረቱም ይህንኑ በመቀበል የጸጥታ ኃላፊው እንዲሰናበቱ አድርጓል።

የአፍሪካ ሕብረትም በዚሁ የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ መሠረት የሕብረቱ የጸጥታ ኃላፊ የታማኝነት ጥያቄ በማንሳትዋ የአፍሪካ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማት ለሜ/ጄኔራል ገብረእግዚአብሔር መብራቱ መለስ የስንብት ደብዳቤ መስጠታቸው ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ