Dr. Debratsion GebreMichael

የጁንታው ሕወሓት መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

ዶ/ር ደብረጽዮን ስኳር ፋብሪካው በጦር ጄት ተደብድቧል ያሉት ሐሰት መኾኑ ተገለጸ

ኢዛ (እሁድ ኅዳር ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 15, 2020)፦ የጁንታው ሕወሓት መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፤ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በጦር ጄት ተደብድቧል በማለት በትናንት ምሽት የሰጡት መግለጫ ሐሰት መኾኑ ተገለጸ።

የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኾኑት አቶ አብርሃም ደምሴ፤ ፋብሪካው በጦር ጄት ተደብድቧል ብሎ ዘራፊው የሕወሓት ቡድን የነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ መኾኑንና ምንም ዐይነት ጉዳት በፋብሪካው ላይ አለመድረሱን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ፋብሪካው የፌዴራል መንግሥቱ መኾኑንና በዓመት አራት ሚሊዮን 840 ሺህ ኩንታል ስኳርና 41 ሚሊዮን 654 ሊትር ኢታኖል እንዲያመርት ታቅዶ የፋብሪካው ግንባት በ2009 ዓ.ም. መጀመሩን የገለጹት አቶ አብርሃም፤ ነገር ግን ፋብሪካው በታቀደለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ በአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታ ማሳደሩን አክለው ገልጸዋል።

የመዘግየቱን ምክንያት፤ የአዋጭነት ጥናት ተጠንቶ ችግሮች እንዳሉበት እየታወቀ በወቅቱ ሥልጣን ላይ በነበረው አካል [ሕወሓት] ውሳኔ ተሰጥቶበት ወደ ሥራ በመግባቱ መኾኑን ገልጸዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ