Dimtsi Weyane

ድምፂ ወያኔ

መከላከያና ፌዴራል ፖሊስ ድምፂ ወያኔ ስቱዲዮ ውስጥ ናቸው

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 4, 2020)፦ የሕወሓት ቡድን ዋነኛ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ጣቢያ በመኾን የሚታወቀው የድምፂ ወያኔ ስቱዲዮ ዛሬ ዓርብ ኅዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በአገር መከላከያ እና የፌዴራል ፖሊስ ተቆጣጥሮታል።

መቀሌ የሚገኘው ይህ ስቱዲዮ የተለያዩ ክፍሎች እና ቁሳቁሶች በሕወሓት ኃይል ጉዳት የደረሰባቸው ስለመኾኑ ስቱዲዮው መያዙን ከሚያመለክተው ምስል መረዳት ተችሏል።

በአሁኑ ሰዓት ድምፂ ወያኔ ስርጭቱ የተቋረጠ ሲሆን፤ ጣቢያው ከትግርኛ ሌላ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በአፋርኛ ቋንቋዎች ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ሲሰራጭበት የቆየ ነው።

ጣቢያው የሚያሰራጫቸው አደገኛ ፕሮፓጋንዳዎች እና ሕዝብን የሚያጋጩ ፕሮግራሞቻቸው ሳቢያ በተደጋጋሚ ከስርጭት ውጭ እንዲኾን ሲደረገ መቆየቱም አይዘነጋም።

ድምፂ ወያኔ በመጀመሪያ በራዲዮ፣ ከዚያም በቴሌቭዥን ፕሮግራም በቅርብ ብቅ ያለ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ40 ዓመታት በላይ በመሰራጨት በብሔራዊ ደረጃ ከሚጠቀሱት ራዲዮና የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ቀጥሎ በረዥም ዕድሜው የሚጠቀስ ነው።

የሕወሓት ቡድን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ሲጠቀምበት የነበረው ይህ ጣቢያ አሁን ላይ ድምፁ መሰማት ማቆሙ ብቻ ሳይኾን ማሰራጫውም በፌዴራል ፖሊስ ሠራዊት ቁጥጥር ላይ ውሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ