የሱዳን ትንኮሳ ብሷል

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር
ድንበር ጥሳ በያዘችው መሬት ላይ ግንባታዎች ማካሔድ ጀምራለች
ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 15, 2021)፦ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ያካሔደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ማጠናቀቁን ካስታወቀ በኋላ፤ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ በመግባት የያዘችውን መሬት ከመልቀቅ ይልቅ፤ በቦታው ላይ ይዞታዋን የማጠናከር ተግባር ስለመቀጠልዋ እየተነገረ ነው።
የሱዳንን ያልተገባ ተግባር ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በትዕግሥት እየተከታተለ እና ሁኔታውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እያረገ ቢኾንም፤ ሱዳን ያለአግባብ በያዘችው ቦታ ላይ አንዳንድ ግንባታዎች እስከማካሔድ መድረሷ አሳሳቢ ኾኗል። (ኢዛ)