Commercial Bank of Ethiopia (CBE) and McKinsey & Company

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ማኬንዚ

ባንኩ በስድስት ወር ውስጥ ከ7.4 ቢሊዮን በር በላይ አትርፏል

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፲ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 17, 2021)፦ ማኬንዚ የተባለው የአሜሪካ ኩባንያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አጠቃላይ አደረጃጀት ለመቀየር የሚያስችለውን ጥናትና አዲስ መዋቅር ለማዘጋጀት የወጣውን ዓለም አቀፍ ጨረታ ማሸነፉ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስድስት ወር ውስጥ ከ7.4 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፍኩ አለ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ ጨረታ መሠረት ወደ 40 የሚደርሱ ኩባንያዎች ተሳትፈው፤ ለመጨረሻ ውድድር አራት ኩባንያዎች ከተለዩ በኋላ፤ ማኬንዚ አሸናፊ መኾኑ ታውቋል።

ማኬንዚ አጠቃላይ የባንኩን አሠራርና አደረጃጀት ይቀይራል የተባለውን ጥናትና ባንኩ የሚሠራበትን አዲስ አሠራር ለማዘጋጀት አሸናፊ የኾነበት ዋጋ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ነው ተብሏል።

ከማኬንዚ ቀጥሎ ሁለተኛውን ዋጋ የሰጠው ኩባንያ ያቀረበው ዋጋ ስድስት ሚሊዮን ዶላር እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ ጨረታውን ያሸነፈው ማኬንዚ በቅርቡ ከባንኩ ጋር የኮንትራት ውል ከተፈራረመ በኋላ ሥራውን ይጀምራል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2013 በጀት ዓመት በስድስት ወር ውስጥ ከ7.4 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ገልጿል።

ባንኩ የግማሽ ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት መሠረት ካስመዘገበው 7.4 ቢሊዮን ብር ሌላ፤ 83 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰቡን ገልጿል። ከ42 ቢሊዮን ብር በላይ አዲስ ብድር በስድስት ወር ውስጥ ያቀረበ ሲሆን፤ ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር አስመልሷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ