የኦሮሚያ ባንክ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ሊኾኑ ነው

አቶ አቤ ሳኖ፣ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን ለቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ኾነው ተሾሙ
አቶ አቤ ሳኖ የሚተኩት አቶ ባጫ ጊናን ነው
ኢዛ (ሐሙስ የካቲት ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 5, 2020)፦ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማኅበር ፕሬዝዳንት በመኾን እያገለገሉ ያሉት አቶ አቤ ሳኖ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ኾነው እንደተሾሙ ተገለጸ።
አቶ አቤ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን ለቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ኾነው የተሾሙት በአቶ ባጫ ጊና ምትክ ነው። አቶ ባጫ ጊና ትናንት የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ኾነው መሾማቸውን መዘገባች አይዘነጋም።
አቶ ባጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ኾነው እያገለገሉ የነበረ ሲሆን፣ በመንግሥት ውሳኔ ኃላፊነታቸውን ለቀው በአምባሳደርነት እንዲሠሩ ተመድበዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ኾነው ዛሬ የተሾሙት አቶ አቤ ሳኖ፤ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ኾነው አገልግለው የነበረ ሲሆን፣ አሁን በድጋሚ የባንኩ ፕሬዝዳንት በመኾን ሥራቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። (ኢዛ)