አቶ ነብዩን ስሑል ሚካኤል (በግራ) እና አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር (በቀኝ)

አቶ ነብዩን ስሑል ሚካኤል (በግራ) እና አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር (በቀኝ)

በምትካቸው አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር ተሹመዋል

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፲ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 17, 2021)፦ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከተቋቋመበት ግዜ አንስቶ የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመኾን ሲያገለግሉ በቆዩት በአቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል ምትክ አዲስ ኃላፊ ተሾመ። የትግራይ ክልል ብልጽግና ጽሕፈት ቤት የመጀመሪያው ኃላፊ በመኾን ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ ነብዩን ተክተው የጽ/ቤት ኃላፊ በመኾን የተሾሙት አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር መኾናቸው የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አስታውቀዋል።

አቶ ነብዩ ስሑል የትግራይ ክልል ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊነታቸውን ቢለቁም፤ በብልጽግና ዋና ጽ/ቤት የአባላት ክትትል እና ድጋፍ ቢሮ ኃላፊ ኾነው ተሹመዋል። የዋናው ብልጽግና ጽ/ቤት እነዚህ ሁለት ሹመቶች አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም፤ የትግራይ ብልጽግና ጽ/ቤት እንደ አዲስ የማደራጀት ሥራ ስለመጀመሩ ይናገራል።

አዲሱ የትግራይ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ በመኾን የተሾሙት አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራርና የጊዜያዊ አስተዳደሩ አስተባባሪ ኾነው ማገልገላቸው ይጠቀሳል።

አቶ ሃፍታይ የፓርቲው የአዲስ አበባ የለውጥ ሥራዎች ክትትል ዘርፍ ኃላፊ በመኾንም ሠርተዋል። በክልሉ የተካሔደው ሕግ ማስከበር ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ፤ የትግራይ ብልጽግና ጽሕፈት ቤቱን በመቀሌ መክፈቱን መዘገባችን አይዘነጋም። የብልጽግና ፓርቲ የመቀሌ ጽ/ቤት ያደረገው ሕወሓት ዋና ጽ/ቤት አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረውን ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ