የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

በኢትዮጵያ ወገን ወደ ኬንያ ለኃይል ሽያጭ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መንገድ ዝርጋታ 448 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦለት የተሠራ ነው

ከሱዳን እና ከጅቡቲ ቀጥሎ ሦስተኛው አገር ትኾናለች

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፲፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 24, 2021)፦ ኬንያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል በመግዛት ከሱዳን እና ከጅቡቲ ቀጥሎ ሦስተኛዋ አገር ለመኾን እየተቃረበች ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዳስታወቀው ወደ ኬንያ የሚዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ መስመር ዝርጋታ የተጠናቀቀ በመኾኑ፤ ኃይሉን ለኬንያ ለመሸጥ ኢትዮጵያ ዝግጁ ነች ተብሏል።

አሁን የሚጠበቀው በኬንያ ወገን ያለው የኃይል ተሸካሚ መስመር ዝርጋታ መጠናቀቅ ብቻ ነው።

የኬንያ መንግሥትም ከኢትዮጵያ ኃይሉን የሚቀበልበትን የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ዝርጋታውን በአራት ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ እየተጠበቀ ነው።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለሱዳንና ለጅቡቲ 100 ሜጋ ዋት ኃይል እየሸጠች ሲሆን፣ ከዚህም የውጭ ምንዛሪ እያገኘችበት ነው።

በኢትዮጵያ ወገን ወደ ኬንያ ለኃይል ሽያጭ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መንገድ ዝርጋታ 448 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦለት የተሠራ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ