የዕለቱ የክብር እንግዳ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሽልማት ሲሰጡ

የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሽልማት ሲሰጡ

ለመጪው ምርጫ 2013 ስኬት ከፖሊስ ብዙ ይጠበቃል

ኢዛ (ቅዳሜ የካቲት ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 27, 2021)፦ እየተበራከቱ የመጡ ወንጀሎችን ለመከላከል በአዲስ አበባ ከተማ በአሁኑ ወቅት የሚገኙትን የፖሊስ ጽሕፈት ቤቶች በእጥፍ ለማሳደግ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን የአዲስ አበባ አስተዳደር አስታወቀ።

የአስተዳደሩ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ እንደገለጸው፤ በዚህ እቅዱ መሠረት 60 የነበሩት የፖሊስ ጣቢያዎች ወደ 120 ከፍ ይላሉ። ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣ ይህ እርምጃው ፖሊስ ወደ ሕብረተሰቡ የበለጠ ተደራሽ ያደርገዋል ተብሏል።

አዳዲሶቹ ፖሊስ ጣቢያዎች እስከ መጋቢት 30 ቀን 2013 ለማቋቋም እየተሠራ መኾኑንም መረጃው ያመለክታል። በእነዚህ ጣቢያዎች ሥርም በተጨማሪነት ማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ይተገበራልም ተብሏል።

የከተማዋን ሰላም ከመጠበቅ አንጻርም ከምርጫ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ችግር እንዳይፈጠር የከተማዋ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ የሚሠራ ሲሆን፣ ከምርጫ ቅስቀሳና ምርጫ ውጤት ጋር ተያይዞ ምንም ዐይነት ችግር እንዳይፈጠር ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ፖሊስ አካዳሚ በሁለት ዙር ያሠለጠናቸውን 1516 ምልምል ፖሊሶችን ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም. አስመርቋል።

የዛሬው ምልምል ፖሊስ ተመራቂዎችን ተገኝተው የመረቁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ናቸው።

የዕለቱ የክብር እንግዳ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፤ ፖሊስ ለመጪው ምርጫ ስኬታማነት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ያስገነዘቡ ሲሆን፣ የከተማዋን ፖሊስ ኮምሽን አቅም ለማጐልበት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

ዛሬ ከተመረቁት 1516 ፖሊሶች ውስጥ 406 ሴቶች ሲሆኑ፤ 1110 ደግሞ ወንዶች ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ