ትግራይ ክልል፣ መቀሌ

ትግራይ ክልል፣ መቀሌ

የልዑካን ቡድኑ ከትግራይ ጊዜ አስተዳደር ጋር ውይይት ያደርጋል

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 28, 2021)፦ በአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና በሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የሚመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ መቀሌ ገብተዋል።

የልዑካን ቡድኑ ዛሬ እሁድ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. መቀሌ የሔደው፤ በትግራይ ከሕግ ማስከበር ሒደቱ ጋር በተያያዘ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መኾኑ ታውቋል። ከእርዳታ ድጋፍ ባሻገር የልዑካን ቡድኑ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የሕግ ማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁ ከተገለጸ ወዲህ የክልል መንግሥታት የተለያየ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የዛሬው የእነ ወይዘሮ አዳነች ጉዞ ደግሞ በከፍተኛ የክልል እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ወደ መቀሌ ያቀኑበት ኾኗል።

በወይዘሮ አዳነችና በአቶ ኦርዲን የተመራው የልዑካን ቡድን መቀሌ ሲደርስ፤ የትግራይ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ከካቢኔ አባላቶቻቸው ጋር በመኾን አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶችም በዚህ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘታቸውም ተገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ