PM Abiy Ahmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

ድጋፉን ያደረጉት ከመጽሐፋቸው ሽያጭና ከደምወዛቸው ነው

ኢዛ (ማክሰኞ የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 2, 2021)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እገዛ የሚውል የ216 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይህንን የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉት ከመጽሐፋቸው ሽያጭ እና ከደምወዛቸው ነው። በመረጃው መሠረት 200 ሺህ ብሩን ከመጽሐፋቸው ከተገኘ ሽያጭ ላይ፣ 16 ሺህ ብሩን ደግሞ ከደምወዛቸው ጨምረው የሰጡ እንደኾነ ተገልጿል።

ይህ ድጋፍ ቃል በገቡት መሠረት የተፈጸመ ነው። በትላንትናው ዕለትም ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለተመሳሳይ ዓላማ የሚውል የ50 ሺህ ብር ድጋፍ በትግራይ ለተጎዱ ወገኖች ማድረጋቸውን መዘገባችን አይዘነጋም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ