የኢትዮጵያ አሮጌ የብር ኖቶች

የኢትዮጵያ አሮጌ የብር ኖቶች

የመጨረው ቀን መጋቢት 10 ቀን ነው

ኢዛ (ቅዳሜ የካቲት ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 6, 2021)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በትግራይ ክልል አሮጌ የብር ኖቶችን የመቀየሪያ ጊዜ የመጨረሻ ያለውን ቀነ ገደብ አስቀመጠ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ክልል የብር ኖት ቅያሬውን ለማጠናቀቅ ከየካቲት 29 ቀን እስከ መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ባሉት 12 ቀናት የብር ኖት ቅያሬ እንዲጠናቀቅ እና በዚሁ መሠረት የየትኛውም ባንክ ቅርንጫፎች በተከፈቱባቸው የክልሉ አካባቢዎች በመሔድ የብር ኖት ቅያሬ እንዲያካሒዱ አሳስቧል።

ይህ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠ የጊዜ ገደብ መኾኑን የሚያመለክተው የብሔራዊ ባንክ መግለጫ፤ በክልሉ ያሉ የባንክ ቅርምጫፎችም በዚሁ መሠረት የብር ቅያሬውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ተግባራዊ እንዲያደርጉም አደራ ብሏል።

በአሁኑ ወቅት ከትግራይ ክልል በስተቀር፤ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች አሮጌው የብር ኖት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

በትግራይ ክልል በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንቅስቃሴ የብር መቀየር ሒደቱ ተስተጓጉሎ የነበረ ሲሆን፤ ከመቀሌ በስተቀር በክልሉ ሁሉም ባንኮች ቅርንጫፎቻቸውን እንዳልነበር ይታወሳል። በዚህም ምክንያት ከመቀሌ ውጭ ያሉ ባንኮች ቅርንጫፎቻቸውን ከከፈቱበት ዕለት ጀምሮ ከ100 ሺህ ብር በታች አሮጌ ብር ላላቸው ተጨማሪ 14 የጊዜ ገደብ መሰጠቱ ይታወሳል።

አሁን ባለው ሁኔታ በክልሉ ይቀየራል ተብሎ የሚታሰበው አሮጌ የገንዘብ መጠን በአብዛኛው የተቀየረ በመኾኑ፤ በክልሉ ያለው የገንዘብ ቅያሬ ገደብ እንዲኖረው ተደርጓል። በዚሁ ምክንያት የተነሳ በክልሉ ያለው አሮጌ የብር ኖት መጠን ጥቂት መኾኑን ታሳቢ በማድረግ፤ በክልሉ የተጀመረውን ብር የመቀየር ሥራ ለማጠናቀቅ ይህ የመጨረሻ የጊዜ ገደብ ሊሰጥ መቻሉን የብሔራዊ ባንክ መግለጫ አመልክቷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ