National Election Board of Ethiopia (NEBE)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ምርጫ 2013)

50 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች፣ ከ152 ሺህ የመራጮች ምዝገባ የሚያካሒዱ ባለሙያዎች እና ከ254 ሺህ በላይ የምርጫ አስፈጻሚዎች ተዘጋጅተዋል

ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 25, 2021)፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ (ምርጫ 2013) ለማካሔድ ከሚጠበቁበት ክንውኖች አንዱ የኾነውን እና ለ30 ቀናት የሚቆየውን የመራጮች ምዝገባ ዛሬ መጀመሩን አስታወቀ።

ቀደም ብሎ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ይጀመራል ተብሎ የነበረው የመራጮች ምዝገባ በተለያዩ ምክንያቶች ተዛውሮ፤ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲጀመር ቦርዱ በወሰነው መሠረት፤ ዛሬ የመራጮች ምዝገባ ተጀምሯል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በመላ አገሪቱ ድምፅ የሚሰጠባቸው 50 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች ያዘጋጀ ሲሆን፤ በእነዚህ ጣቢያዎች ከ152 ሺህ በላይ የመራጮች ምዝገባ የሚያካሒዱ ባለሙያዎች እና ከ254 ሺህ በላይ የምርጫ አስፈጻሚዎች ተዘጋጅተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመራጮች ምዝገባ ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ነፃ የስልክ መስመር ከሰኞ ጀምሮ አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ