National Election Board of Ethiopia (NEBE)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ምዝገባው ከዛሬ ወደ መጋቢት 16 ተዛውሯል

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 1, 2021)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩን አገራዊ ምርጫ 2013 ለማካሔድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለመራጮች ምዝገባ የተያዘውን ቀን በሃያ አራት ቀናት አራዘመ።

ቦርዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የመራጮች የምዝገባ ቀን ብሎ ይዞ የነበረው በዛሬው ዕለት የካቲት 22 ቀን ሲሆን፤ አሁን ግን ወደ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲዛወር ወስኗል።

የመራጮች የምዝገባ ጊዜ እንዲራዘመ የተወሰነባቸውን ምክንያቶች በመግለጫው ያካተተው ቦርዱ፤ “ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ተግባራትን ማከናወን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል የምርጫ ክልል ቢሮዎች ዝግጅት መዘግየት እና አስፈጻሚዎች ሠልጥነው ከተሰማሩም በኋላ ቢሆን ቢሮዎች ዝግጁ ኾነው ባለመገኘታቸው የቢሮ መከፈት መዘግየቱ፣ በተወሰኑ ክልሎች አስፈላጊው ቢሮዎች ተዘጋጅተው ባለማለቃቸው የእጩዎች ምዝገባ በጊዜ ሰሌዳው መሠረት መጀመር አለመቻሉ እና ለሁለት ዙር መከፈሉ፣ ለምርጫ ቁሳቁሶች ስርጭት የትራንስፖርት እጥረት እና የገለልተኛ አስፈጻሚዎች ምልመላ ሒደት ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጊዜ የሚወስድ ተግባር መኾኑ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።” በማለት አስረድቷል። በዚህ ውሳኔው መሠረት የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከመጋቢት 16 ቀን እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ይከናወናል ተብሏል። የቦርዱን ሙሉ መግለጫ አስነብበኝ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ