የአማራ ሕዝብ ተቃውሞ

የአማራ ሕዝብ ተቃውሞ፣ ሐሙስ ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም.

ባሕር ዳር ፈዝዛ ዋለች

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. April 22, 2021)፦ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈጸምውን ዘር ተኮር ጥቃት በመቃወም በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች እየተሰሙ ያሉት ትዕይንተ ሕዝብ ዛሬም በተለያዩ ከተሞች ሲካሔድ ውሏል።

ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ዘር ተኮር ጥቃቱን በመቃወም የጎንደር፣ የቆቦ፣ ደብረ ብርሃን መራዊ፣ ሞጣ፣ ደብረ ታቦር፣ መርሳ፣ ኢንጅባራ እና የመሳሰሉት ከተሞች ተጠቃሸ ናቸው።

የተቃውሞ ድምፆቹን ያሰሙት ሰልፈኞች ሰልፋቸውን በሰላማዊ መንገድ ያከናወኑ ሲሆን፣ የተለያዩ መፈክሮች የተሰሙበት ነው። ከእነዚህ ውስጥ “የታገስነው ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ብለን እንጂ ፈርተን አይደለም”፣ “ሕዝብ እና ሕዝብ መቼም ቢኾን አይጣሉም፤ ጥገኛ ፖለቲከኞች ሴራችሁን ይዛችሁ ጥፉ”፣ “ለአማራ መሳደድ መነሻ የኾነው ሕገመንግሥት በአስቸኳይ ይሻሻል”፣ “ሕፃናት መግደልና ከተማ ማፍረስ ጀግንነት አይደለም”፣ የሚሉና መሰል መፈክሮች የተስተጋቡበት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ጠዋት በባሕር ዳር ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች መንገድ ተዘግተው ነበር። በድንጋይና በእንጨት መንገዶቹን የዘጉ ወጣቶችና የጸጥታ ኃይሎች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮም እንደነበር ተገልጿል።

ኾኖም ከቆይታ በኋላ መንገዶቹ እንዲከፈቱ ተደርጓል። ነገር ግን በተፈጠረው ክስተት ንግድ ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ ተስተጓጉሎ የዋለ ሲሆን፤ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴም በእጅጉ ቀንሶ መንገዶች ባዶ ኾነው ታይተዋል። አሁን ላይ ከተማዋ፣ ሰላም ነች ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ