የኮሚሽነር አበረ አዳሙ የቀብር ሥርዓት ተፈጸመ
የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ሥርዓተ ቀብር ሐሙስ ሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በባሕር ዳር ተፈጸመ
ቀብራቸው በባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል
ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 6, 2021)፦ በድንገተኛ ሕመም መሞታቸው የተነገረው የአማራ ክልል የቀድሞ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የቀብር ሥርዓታቸው ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።
የቀድሞው ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስከሬን ሥርዓተ ቀብሩ ወደሚፈጸምበት ቤተ ክርስቲያን ሽኝት ሲደረግለት እና በሥርዓተ ቀብሩ ላይ ቤተሰቦቻቸው፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ሚኒስትሮች፣ እንዲሁም የሥራ ባልደረቦቻቸው ተገኝተዋል።
አስከሬኑ በወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት ተሸኝቶ፤ ሥርዓተ ቀብሩ እንደተፈጸመ ለማወቅ ተችሏል።
ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ባለትዳርና የሁለት ወንዶች ልጆች አባት ነበሩ። (ኢዛ)



