Somali region, Ethiopia

ሶማሌ ክልል

የምርጫ ክልሎቹ ያልተገባ ተግባራት የተፈጸመባቸው ናቸው ተብሏል

ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 8, 2021)፦ ከምርጫ ምዝገባ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ አቤቱታ እየቀረበበት መኾኑ በተነገረለት በሶማሌ ክልል፤ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ የመራጮች ምዝገባ በጊዜያዊነት እንዲቆም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መወሰኑን አስታወቀ።

ቦርዱ ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ ሒደት ላይ ከፍተኛ አቤቱታ እየቀረበበት መኾኑን ገልጾ፤ ይህንን አቤቱታ ተከትሎ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ እንዳመጣ አመልክቷል።

ከመራጮች ምዝገባ ጋር ተያይዞ ለቦርዱ ከደረሱ አቤቱታዎች መካከል፤ የመራጮች ምዝገባ ካርዶች የማይገባቸው ሰዎች እጅ ገብቷል፣ ከምርጫ ጣቢያ ውጭ ካርዶች ሲታደሉ ነበር የሚሉ ይገኙባቸዋል።

ከዚህም ሌላ ያልተሞሉ የመራጮች ምዝገባ ካርዶች ምዝገባ ካርዶች ዝቅተኛ የመንግሥት እርከን ለሚባሉት የቀበሌና የወረዳ እና እጩዎች ተሰጥተዋል የሚል እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደጋፊ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ዜጐች እንዳይመዘገቡ ክልከላ ተደርጐባቸዋል የሚሉም አቤቱታዎች ቀርበዋል።

ሌሎችም ያልተገቡ ተግባራት ተብለው የተጠቀሱ አቤቱታዎችን የጠቀሰው ቦርዱ፤ አቤቱታዎችን መርምሮ አቤቱታ የቀረቡባቸው የምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ በጊዜያዊነት እንዲቆም ውሳኔ አሳልፏል።

ቦርዱ የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባን በተመለከተ የሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ