አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይቅርታ ጠየቁ

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 10, 2021)፦ ትናንት በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ሊካሔድ የነበረው የረመዳን የአፍጢር ሥነ ሥርዓት ነገ በመስቀል አደባባይ በመንግሥት ወጪ እንዲካሔድ ተገለጸ።

ትናንት እሁድ ግንቦት 1 ቀን 2013 ዓ.ም. በመጨረሻው ሰዓት ከጸጥታ ሥጋት ጋር በተያያዘ እንዲታጎል የተደረገው የአፍጢር ሥርዓቱ በሙስሊሙ ሕብረተሰብም ኾነ በሌሎች የእምነት ተከታዮች ዘንድ ተቃውሞ ያስነሳም ኾኗል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በይፋ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፤ ፕሮግራሙ ሊስተጉጎል የቻለው በጸጥታ ሥጋት እንደኾነ አስታውቆ ነበር። ይህንኑ ተከትሎ ማምሻውን በተሰማ መረጃ፤ ነገ በመንግሥት ወጪ የአፍጢር ፕሮግራሙ ይካሔዳል ተብሏል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ይቅርታ ባሉበት መልእክታቸው፤ የኢትዮጵያ አደባባዮች የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኾናቸውን አስታውሰው፤ የትናንቱን አፍጢር የተስተጓጎለው ወቅታዊ የደኅንነት እና የጸጥታ ሁኔታን ከግምት በማስገባት የቦታው ስፋት እና ርዝመት ውስን እንዲኾን ባቀረብነው ሐሳብ አዘጋጅ ኮሚቴው ባለማመኑ ብቻ መኾኑ ግልጽ እንዲኾን እንፈልጋለንም ብለዋል። አፍጢሩንም ለመከልከል እንዳልነበር አክለው ገልጸዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ