ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተጨማሪ የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ተሰጠ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ምርጫ 2013)
ምዝገባው እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ተራዝሟል
ኢዛ (ረቡዕ ግንቦት ፲፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 19, 2021)፦ ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ 2013 የመራጮች ምዝገባ ቢጠናቀቅም፤ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ አሳልፏል።
ቦርዱ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገዛ ጊዜ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጥ በወሰነው መሠረት እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ተማሪዎቹ ምዝገባውን ያካሒዱ ብሏል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመራጭነት ምዝገባውን የሚያካሒዱት ቦርዱ ባዘጋጀው የኢንተርኔት አድራሻ ነው። (ኢዛ)



