Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)

ታላቁ የህዳሴ ግድብ

ግብጽ ኢትዮጵያ ወደምታራምደው ሐሳብ እየመጣች ነው

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፲፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 20, 2021)፦ ከትናንት በስቲያ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ላይ የሰጡትን አስተያየት የኢትዮጵያን አቋም የሚደግፍና የውኃ ሙሌቱ የግብጽ ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ እንደማያሳድር መግለጻቸውም ጥሩ ጅማሮ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ገለጹ።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ፤ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳሚ ሹክሪ በግድቡ የውኃ ሙሌት ዙሪያ ቀደም ሲል ግብጽ ታራምድ የነበረውን አቋም በመቀየር ኢትዮጵያ የምታራምደውን አቋም ወደ መደገፍ መሸጋገሯን ያመለክታል ብለዋል።

ግብጽ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ዙሪያ ከኢትዮጵያ የተለየ አቋም ይዛ፤ ሙሌቱ እንዳይካሔድ በብርቱ ስትሞግት የነበረ ሲሆን፤ ከትናንት በስቲያ ግን ከዚህ ሐሳብ በተለየ የውኃ ሙሌቱ የግብጽን ፍላጎት የማይጐዳ ነው ማለታቸው ትልቅ ለውጥ ነው ተብሏል።

ዛሬም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህንን የግብጽን ሐሳብ በመልካም በመውሰድ ጥሩ ጅማሮ ነው ለማለት በቅቷል።

ግብጽ ግትር ኾና በቆየችበት የግድቡ የውኃ አሞላል ሒደት ላይ አቋሟን እንዲህ ማለስለስዋ ግን እንዴት ሆነ? የሚል መጠየቅ ማስነሳቱ አልቀረም። ምንም ይሁን ምን አሁንም የግብጽን ጉዳይ በዚህ አገላለጽም ብቻ ማመን ከባድ ነው የሚሉ አስተያየቶች ግን ከተለያዩ ወገኖች እየተሰነዘሩ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ