USA and Ethiopian flags

የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ባንዲራዎች

አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ ለመጣል እየተዘጋጀች ነው

ኢዛ (ዓርብ ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 21, 2021)፦ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ በትር ለማሳረፍ የጀመረችውን ጫና ያጠናክርልኛል ያለችውን ማእቀብ ለመጣል እየተዘጋጀች ስለመኾኑ እየተሰማ ነው።

በአሜሪካ እና መሰል ምዕራባውያን አገሮች ላይ ኢትዮጵያውያን እጃችሁን አንሱ በሚል በተለያዩ አቅጣጫዎች ድምፃቸውን እያሰሙ ቢኾንም፤ አሜሪካ በተለያዩ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እቀባና መሰል እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት እያደረገች ነው ተብሏል።

ከዚህም ሌላ በዓለም ባንክ በኩል በኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ እንዲጣል ታደርጋለች እየተባለ መኾኑም ታውቋል።

በፍሪን ፖሊሲ ዘገባ ይህንን ማእቀብ አሜሪካ በቀናት ውስጥ አጽድቃ ተግባራዊ ታደርጋለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የዚህን ያህል ጠንክራ የወጣችበትና ጫና ለማሳደር እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ