Hands off Ethiopia

“ብሔራዊ ክብር በሕብር”

የአሜሪካና የምዕራባውን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ የሚደርጉትን ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያውያን ተቃወሙ

ኢዛ (ዓርብ ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 21, 2021)፦ አሜሪካ እና ምዕራባውያን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ እያራመዱ ያሉትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

“ብሔራዊ ክብር በሕብር” በሚል ኢትዮጵያውያን የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት በመቃወም በየአካባቢው የተሰሙት ድምፆች የተለያዩ መፈክሮች የታዩበትና መልእክቶች የተላለፉበት ነበር።

“እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ”፣ “ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ የሚያሳድሩት ተጽእኖ የአገርን ሉዓላዊነት የሚጥስ ነው”፣ “ግድቡ የኔ ነው”፣ “እንደ ትናንቱ ዛሬም ሉዓላዊነት አገር እናስቀጥላለን”፣ “ኢትዮጵያን አትንኳት”፣ “ሉዓላዊነታችንን አክብሩ”፣ “ምርጫችን የራሳች”፣ “ኢትዮጵያ ተምርጣለች”፣ “አንድ ነን”፣ የሚሉና ሌሎች ተመሳሳይ መልእክቶች ያላቸው መፈክሮች ጎልተው ታይተዋል።

በሰላማዊ ሰልፍ ጭምር የታጀበው የውጭ ጣልቃ ገብነትን የተቃወሙት የዛሬው ሰልፈኞች፤ ለወንድማማችነት እንጂ ለጣልቃ ገብነት ቦታ የለንም የሚል መልእክት ተላልፏል።

የዛሬው ሰልፍ እንዲህ ካለው ገጽታ ባሻገር በአዲስ አበባ በሚገኙት እንደ አሜሪካ እና እንግሊዝ ኤምባሲዎች በመሔድ የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ የያዘ ደብዳቤ ለማስገባት ያለመ ጭምር ቢኾንም፤ ኤምባሲዎቹ በዛሬው ዕለት ሥራ እንዳማይሠሩ ቀድመው ያስታወቁና ዝግ በመኾናቸው፤ ለኤምባሲዎቹ ሊሰጥ የነበረው ደብዳቤ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መደረጉ ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ