National Election Board of Ethiopia (NEBE)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ምርጫ 2013)

መንግሥት የሚመሠርተው ፓርቲ ዛሬ ይለያል

ኢዛ (ቅዳሜ ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 10, 2021)፦ በተለያዩ መመዘኛዎች በኢትዮጵያ ከተካሔዱ ምርጫዎች በተሻለ ሁኔታ ተካሒዷል ተብሎ የሚታመንበትን የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እስካሁን ጊዜያዊና የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶችን በተከታታይ ሲገልጽ የቆየ ሲኾን፣ ዛሬ ግን በእጁ ያሉትን አጠቃላይ የምርጫ ውጤቶች ይገለጻሉ።

ዛሬ ይፋ የሚደረገው የምርጫ ውጤት በተረጋገጠ ሁኔታ በምርጫ አሸናፊ በመኾን መንግሥት ሊመሠርት የሚችለው ፓርቲ የሚታወቅበት እንደሚኾን ይታመናል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ