ቴድሮስ ኃይለ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ከደርጉ የገበሬ ማኅበር ካድሬዎች በገራገርነቱ የሚታወቀው የጎጃሙ ቆምጫምባው እንደዋዛ አለ ተብሎ ከሚነገርለት አባባል አንዱ፤ ጋዜጠኛ ”ለመሆኑ ክቡርነትዎ የአሜሪካንን ኢምፔሪያሊዝም እንዴት ይመለከቱታል?” ሲል ለጠየቃቸው፤ ጓድነታቸው ባልተንዛዛ አማርኛ ”የጎሪጥ ነው የማየው” ሲሉ ቆፍጠን ያለ መልስ እንደሰጡ በቀልድ መልክ ሲነገርና፤ ለአንዳንድ ግልገል ካድሬዎችና አድርባዮችም ጭፍን አቋምና ባዶ ፕሮፓጋንዳ እንደ ምሳሌ ሲቀርብ ይስተዋላል።

 

ከጭፍን ካድሬዎችና ከእበላ ባይ ጭፍሮች ያልተላቀቀው የሀገራችን ፖለቲካ ይትባህል ዛሬም ከትናንቱ በባሱ የፖለቲካ ደናቁርትና ምንደኞች ሳይላቀቅ ሦስት አሥርተ ዓመታት አልፈውታል። ታዲያም ከትናንት የዋህ የለብለብ ካድሬዎች የዛሬዎቹ ሲነፃፀሩ አንዳንዴ ገራገሮች ባይጠፉም፤ በአብዛኛው ግን ’እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል’ አለች እንደተባለው እንስሳ ሆዳቸውን ያስቀድሙና ዓይናቸውን በጨው አጥበው በድርቅና ጥፋት መሆኑን አውቀው ለጥቅም የተሰማሩ ’የአባትህ ቤት ሲፈርፍ አብረህ ዝረፍ’ የሚለውን ሠይጣናዊ ጥቅስ መመሪያ በማድረግ፤ የሀገር ውድቀት የህዝብ ጉስቁልና ዋይታና ሰቆቃ አይተው እንዳላዩ በመምሰል በወገናቸው ላይ ለሚፈፀመው ኢ-ፍትሃዊ ተግባር ተባባሪ በመሆን የተሰማሩ ካድሬዎችና ለዚህ የግፍ ተግባር ለመሰማራት የሚቋምጡ ጭፍሮች በሀገርም በውጭው ዓለምም እየተበራከቱ በመሄድ ላይ ናቸው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ