“ምርጫው ይደገም” ተቃዋሚዎች

“የምርጫ ሥርዓትን የተከተለ አይደለም” ስቴት ዲፓርትመንት

በግል በብቸኝነት ለፓርላማ ያለፉት ከእግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ኢህአዲግ በጉልበት ያነሳቸው ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ናቸው

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 18 ቀን 2002 ዓ.ም. May 26, 2010)፦ በኢትዮጵያ ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. በተካሄደው ‘ምርጫ’ ገዥው ፓርቲ በቅድመ ምርጫ ቆጠራ ማሸነፉን ካወጀ ወዲህ በተቃዋሚዎች፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና በአውሮፓ ታዛቢዎች ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑ ተነገረ። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት መግለጫ አውጥቷል።

 

የአቶ መለስ ምርጫ ቦርድና ኢህአዲግ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ … የተሟላ ድምፅ ማግኘቱን ካወጀ በኋላ፤ በዋዜማው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ደርጅት ምርጫው ፍፁም የምርጫ ደረጃን ያልጠበቀ ነው በማለት ባወጣው መግለጫ ሲገልጽ፤ የአውሮፓ ታዛቢዎች ቡድን ደግሞ ‘ምርጫው’ ገዥው ፓርቲ ሙሉ በሙሉ የመንግሥትን ገንዘብ፣ መገናኛ ብዙኀንና ሙሉ ኃይል የተጠቀመበትና ሚዛናዊ ያልሆነ ነው ሲል ተችቶታል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው ምርጫው ፍትሃዊነት የጎደለውና ኢህአዲግ አምባገነንነቱት ይፋ ያደረገበት መሆኑን ገልጸዋል።

 

የግንቦት 18 ቀን 2002 ዓ.ም. የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ያወጣውን መግለጫ ለማውገዝ ወደ መስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ ብዙ የገዥው መደብ ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን፤ ገዥው ፓርቲ ለሚቀጥለው አምስት ዓመት ሀገሪቷን ለመግዛት ያለውን ቁርጠኝነት ይፋ አድርጓል።

 

የስምንት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው መድረክ፤ የምርጫው ሂደት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራና ውጤቱን የማይቀበለው መሆኑን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። በኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል የሚመራው መኢአድ በበኩሉ ድጋሚ ምርጫ እንዲደረግ ለምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የአቶ ልደቱ አያሌው ኢዴፓ አመራር አባላቱ ከምርጫ ቦታቸው ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ ገብተው ሲጠናቀቁ የፊታችን ሰኞ መግለጫ እንደሚያወጡ አስታውቀው፤ ምርጫው የኢትዮጵያን የምርጫ ሂደት ለ19 ዓመታት ወደኋላ የመለሰ ነው ሲሉ ተደምተዋል።

 

ይህ የዘንድሮው ምርጫ “የኢህአዲግ ብቸኛ ቅርጫ” የሚል ስም የወጣለት ሲሆን፤ አብዛኛውን በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ያስቆጣ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

 

የአቶ መለስን ንግግር በሚመለከት ተቃዋሚዎች ቀድሞ የተዘጋጀና ለማስፈራራት ሆን ተብሎ የተቀናጀ ሂደት ነበር ብለውታል።

 

በአዲስ አበባ ከተማ ድምፅ ከተሰጠባቸው ጣቢያዎች መካከል 6ቱን ለናሙና ወስዶ መገምገም እንደሚቻል የጠቆሙ የምርጫ ታዛቢዎች ናሙናው የድምፅ ኮታ እንዴት ተሰጥቶ እንደነበር ጠቋሚ ከመሆኑም በላይ፤ ናሙናው አዲስ አበባ በአብዛኞቹ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ተመሳሳይ ውጤት ታይቶባቸዋል። የምርጫ ካርድ ወስደው ለታሪክ በእጃቸው ያስቀሩ ዜጎች እንዳሉ የተረጋገጠ ሲሆን፤ በአብዛኞቹ ጣቢያዎች ለኢህአዲግ የተሰጠው ድምፅ ሦስት መቶ ቤት፣ ለመድረክ ሁለት መቶ ቤት፣ ለኢዴፓ ሃያ ቤት፣ ለመኢአድ ደግሞ አስር ቤት መሆናቸው አስታውቋል።

 

ፓርቲዎች የምርጫ ጣቢያዎችና ያገኙት ድምፅ ናሙና

የፓርቲ ሥም ም/ጣ1 ም/ጣ2ም/ጣ3 ም/ጣ4 ም/ጣ5 ም/ጣ6 ደረጃ 
ኢህአዲግ323 323 332 343 358 358 1ኛ 
መድረክ236 264 265 294 296 298 2ኛ 
ኢዴፓ21 21 22 23 23 23 3ኛ 
መኢአድ11 12 12 13 13 15 4ኛ 

 

“የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር” (ኢህአዲግ) ከ547ቱ የፓርላማ መቀመጫዎች 499ኙን “አግኝቷል” ተብሏል። እስከአሁን ተገኝተዋል ከተባሉት 536 ያህል ድምጾች መካከል ቀሪዎቹን 35 ድምጾች የገዥው ፓርቲ “አጋር” የተባሉት ፓርቲዎች ጠቅልለዋል። ከሁለቱ ቀሪ መቀመጫዎች ውስጥ አንዱ የመድረክ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በግል የተወዳደሩት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ መሆናቸው ተገልጿል። ዶ//ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በባለሀብቶቹ በእነ ሼህ አላሙዲን እና በአቶ አብነት ግፊትና በኢህአዲግ ተባባሪነት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት መነሳታቸው ይታወቃል።

 

ገዥው ፓርቲ በብቸኝነት የሀገሪቱን ፓርላማ መቆጣጠሩ የደርግ ዘመንን ሁናቴ ያስታውሳል ሲሉ ኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል ተናግረዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ