ቅንጅት የበጀት ድጎማ እንዲለቀቅ ጠየቀ
Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 12 ቀን 2001 ዓ.ም. November 21, 2008)፦ መንግሥት በፓርላማ መቀመጫ ላላቸው ፓርቲዎች እሰጣለሁ ያለውን የበጀት ድጎማ አለመልቀቁ፣ የፓርቲዎችን የትግል እንቅስቃሴ ለማዳከም የተጠቀመበት ዘዴ መሆኑን የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ።
በአቶ አየለ ጫሚሶ የሚመራው ቅንጅት፣ ”የቅንጅት ዓላማና የህዝብ ትግል በገዢው ፓርቲ በተጽዕኖ ሊያፍን አይችልም” በሚል ርዕስ ባወጣው ባለ 13 ነጥብ መግለጫ፣ መንግሥት በፓርላማ መቀመጫ ላላቸው ፓርቲዎች የበጀት ድጎማውን እንዲለቅ ጥሪ አቅርቧል።
ፓርቲው በመግለጫው የሙስና መበራከት፣ የኑሮ ውድነት፣ ከሥራ ገበታቸው የሚባረሩ ሠራተኞችን እና በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል።



