Artist Debebe Eshetu's bookEthiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 24 ቀን 2000 ዓ.ም. April 2,2008) የቅንጅት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው አርቲስት ደበበ እሸቱ "የእምነቴ ፈተና" በሚል ርዕስ ያሳተመው መጽሐፍ አሜሪካን ውስጥ ዋሽንግተን ዲሲ ገበያ ላይ መዋሉን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ጠቆሙ።

 

"የእምነቴ ፈተና" የመጽሐፉ ዋና ርዕስ ሲሆን፣ ንዑስ ርዕሱ ደግሞ "ከምርጫ 97 - ቃሊቲ እስራትና ..." የሚል ነው። ምርጫ 97ን ተከትኮ ምን ተፈጠረ?፣ የቅንጅት አመራሮችን ማሰር ለምን አስፈለገ?፣ ከምርጫ በፊት፣ በኋላና ቃሊቲ የተሰየመው ፍርድ ቤትስ ምን ይመስል ነበር?፣ ... ለሚሉና ተመሳሳይ ጥያቄዎች አርቲስት ደበበ የራሱን ዕይታና ምላሽ በመጽሐፉ ላይ እንደሰጠ ለማወቅ ተችሏል።

 

ከዚህም በተጨማሪ በመጽሐፉ የሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ የዓላማና የሀገር ፍቅር እምነቴ በፈተና ውስጥ፣ የምርጫ ዘመቻ፣ ከስብሰባዎች ናሙናዊ ዕይታ፣ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ፣ ወደ ቅንጅት ጉዞ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ስለመቀናጀት፣ ገዥው ፓርቲና የምርጫ ስለቱ ምላሽ፣ የፖለቲካ ዳጥ፣ ወደ ወልቂጤና አካባቢው፣ ሚያዝያ 29፣ ... የሚሉት የሚጠቀሱ ናቸው።

 

አርቲስት ደበበ በዚሁ መጽሐፉ ውስጥ ከምርጫው እስከ ቃሊቲ እስር ቤት የነበረውን የቅንጅትን፣ የሀገሪቱን ፖለቲካ፣ የኢህአዴግን ሁኔታ፣ ... የራሱን ዕይታ አስፍሯል። የመጽሐፉ ዋጋ 20 የአሜሪካን ዶላር እንደሆነ ለማወቅ ችለናል። በመጽሐፉ አንዳንድ ፎቶግራፎችም ተካትተዋል።

መሐመድ፣ ዶ/ር ብርሃኑ፣ ሻለቃ አድማሱና ገንጠል ብለው ያሉት አቶ በድሩ አደም። ሻለቃ አድማሱና በድሩ የመኪናው ችግር እንደማይመለከታቸው ዓይነት ለዶ/ር ብርሃኑና ለመሐመድ የመግፋቱን ጣጣ ትተውት

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ