ለቅጣት ውሳኔ የፊታችን ዓርብ ተቀጠረ

Teddy Afro

Ethiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 22 ቀን 2001 ዓ.ም. December 01, 2008)፦ ለስምንት ወራት ሰው በመኪና ገጭቶ በማምለጥ ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ ዛሬ ኅዳር 22 ቀን በመጥፎነቱ በሚታወቀው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ጥፋተኝ ተብሎ እንደተወሰነበት ችሎቱን የተከታተሉ የአዲስ አበባ ምንጮቻችን አስረዱ።

 

 

ችሎቱ አሳዛኝና ዳኛው የክርክሩን ሂደት ራሳቸው በፈለጉት መንገድ ለመተርጎም እንደፈለጉ በማየት የተበሳጩ ወገኞች እንዳሉት፤ ዳኛ ልዑል የቀረቡትን የመከላከያ ክርክሮች በቅንነት ለመተርጎም አለመቻላቸው እጅግ እንዳሳዘናቸው ጠቁመዋል።

 

የቅጣት ማቅለያ ሃሳብ እንዲያቀርቡ የተጠየቁት የቴዎድሮስ ካሳሁን ጠበቃ፤ "ደንበኛዬ ጥፋተኛ አይደለም በማለት ስንከራከር በመቆየታችን የጥፋት ማቅለያ ለማቅረብ አልተዘጋጀንም" በማለት የመለሱ ሲሆን፣ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንም "በሐቅ ለማይሠራ ፍርድ ቤት ከዚህ በላይ የማቀርበው የማቅለያ ሃሳብ የለም" ሲል መደመጡን በስፍራው የተገኙ ታማኝ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

 

ዳኛው ልዑል ገ/ማርያም የቅጣት ውሳኔውን ለመስጠት ለፊታችን ዓርብ ኅዳር 26 ቀን 2001 ዓ.ም. መቅጠራቸውን ለማወቅ ችለናል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ