አንድነት ፓርቲ የወ/ት ብርቱካንን መታሰር ኮነነ
የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን መታሰር አስመልክቶ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ “የብርቱካን ሚደቅሳ እንደገና መታሰር በሀገራችን እየታየ ያለውን የሕግ ጥሰት አጉልቶ ያሳያል፤ ከሕግ በላይ መሆን ይቁም!” በማለት መግለጫ አውጥቷል። በዚሁ መግለጫው የሊቀመንበሯ መታሰር በሳቸው ላይ ሳይሆን በፓርቲው ላይ ያነጣጠረ ነው ሲል ኮንኖታል።
ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፤ ወ/ት ብርቱካን ተናገሩት በተባለው ንግግር ምክንያት ቦርዱ ይቅርታቸውን ሊያነሳው አይገባም ነበር፤ ቦርዱ ንግግሩ ጥፋት ነው ብሎ ቢያምንም እንኳን በይቅርታ ሕጉ መሰረት መልስ እንዲሰጡበት የ20 ቀናት ጊዜ ሊሰጣቸው ይገባ ነበር ብሏል በመግለጫው። ነገር ግን ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ሊቀመንበሯን ለእስር መዳረግ በፓርቲው ላይ ያነጣጠረ ነው ሲል ኮንኖታል።
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ያወጣውን ሙሉ መግለጫ አስነብበኝ።



