Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 18 ቀን 2001 ዓ.ም. January 26, 2009)፦ ዝነኛው የሙዚቃ አቀንቃኝና የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲ የቴዎድሮስ ካሳሁን የይግባኝ ችሎት ዛሬ መታየት መጀመሩ ታወቀ።

 

ቴዲ አፍሮ ኅዳር 26 ቀን የ18 ሺህ ብር ቅጣትና የስድስት ዓመት ጽኑ እስራት በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተፈረደበት በኋላ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው የይግባኝ ጥያቄ መሰረት ዛሬ ሰኞ ጥር 18 ቀን 2001 ዓ.ም. የቀረበ ሲሆን፣ በይግባኝ ጠያቂው ቴዎድሮስ ካሳሁንና በዓቃቢ ሕጉ መካከል የክርክር ሃሳቦች ተሰምተዋል።

 

ዓቃቢ ሕግ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጥው ውሳኔን ትክክለኛነት ያስረዳ ሲሆን፣ 13 የሚሆኑ ምክንያቶችንም ያስቀመጠ ሲሆን፣ የቴዲ ጠበቃ አቶ ሚሊዮን አሰፋ ውሳኔውን በመቃወም ደንበኛቸው በነፃ እንዲለቀቅ ጠይቀዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ