Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 19 ቀን 2001 ዓ.ም. January 27, 2009)፦ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የታሰረችበትን አንደኛ ወር በአጋርነት በማሰብ የሻማ መብራትና የግጥም ስነሥርዓርት ነገ በፓርቲው ጽሕፈት ቤት ይካሄዳል። ፕሮፌሠር መስፍን ጽሑፍ ያቀርባሉ።

 

ነገ ጥር 20 ቀን በሚካሄደው የሻማ ምሽት ላይ የተለያዩ ጽሑፎችና የፓርቲው አመራር መልዕክቶች የሚተላለፉ ሲሆን፣ ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም የብርቱካንን እስር ሁኔታ የመጨረሻ ሰዓት በሚመለከት ያዩትን በምስክርነት በተወዳጁ ብዕራቸው ጽሑፍ እንደሚያቀርቡ ለማወቅ ችለናል።

 

የአንድነት ፓርቲ መሪ እንድትፈታ የሚጠይቅ ሀገር አቀፍ ሠላማዊ ሰልፍ ለመጥራት ፓርቲው በዝግጅት ላይ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ የወ/ት ብርቱካን ጠበቃ አቶ ተስፋዬ ደረስ ደንበኛቸውን ለማነጋገር ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውንና በቅርቡ ሊሳካ እንደሚችል የፓርቲው ቃል አቀባይ በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ አስረድተዋል።

 

ወ/ት ብርቱካን ከታሰረች ነገ ጥር 20 ቀን አንደኛ ወር ይሆናታል። ሂደቱን ተከታትለን እናቀርባለን።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ