‘ለአክስቷ ልጅ የተፈቀደው በስህተት ነው’ ፖሊስ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ የካቲት 03 ቀን 2001 ዓ.ም. February 10, 2009)፦ ከሽማግሌዎቹ አንዱ በሆኑት ፓስተር ዳንኤል ቢሮ ስትወጣ በታጠቁ ሰዎች ተይዛ ወደ እስር ከተጣለች 41ኛ ቀኗን ያስቆጠረችው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በአክስቷ ልጅ እንዳትጎበኝ ተከለከለች።

 

የማረሚያ ቤት ፖሊስ እንዳስታወቀው ከአሁን በፊት ተፈቅዶ የነበረው በስህተት በመሆኑ ከእሁድ ዕለት ጀምሮ የብርቱካን እናት ያሳደጓት የአክስቷ ልጅ መጠየቅ የማትችል መሆኗን ለማረጋገጥ ችለናል።

 

በአሁኑ ሰዓት እናቷና ሕፃን ልጇ ብቻ የሚጎበኗት ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ሦስተኛ ሰው እንዲጎበኛት የተፈቀደው የ72 ዓመት እናቷ ለልጃቸው ይዘውት የሚገቡት ምግብ ውሃና የተለያዩ ነገሮችን ተሸክመውና ሕፃን ልጅ ይዘው በቃሊቲ እስር ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ረጅም መንገድ ይጓዙ ስለነበር፤ ሁኔታው ያሳዘናቸው ፖሊሶች ወጣቷ የአክስቷ ልጅ እንድታግዛቸው አድርገው ነበር። ካለፈው እሁድ ጀምሮ ከበላይ በመጣ ትዕዛዝ የተፈቀደው በስህተት በመሆኑ ከእናቷና ከልጇ ውጭ ማንም ሰው ወ/ት ብርቱካንን ሊጎበኝ እንደማይችል አስታውቋል።

 

በዚህች ወጣት የፖለቲካ መሪ ላይ ከማስፈራራት ጀምሮ እስከአሁን በእስር እስከወደቀችበት ጊዜ ድረስ አገዛዙ የሚወስደው አቋምና እርምጃ እጅግ የተምታታ ነው የሚሉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ፤ እስረኛ የሆነችው ይቅርታው ተነስቶ ነው ቢባልና ፍርደኛ እስረኛ ከሆነች በቤተሰብና ጠበቃ የማትጠየቅበት ምክንያት ግራ የሚያጋባ ከመሆኑም በላይ፤ አገዛዙ 'የፖለቲካ እስረኛ አይደለችም' እያለ፤ በሌላ በኩል እንዲህ አይነት ዓይን ያወጣ ተጽዕኖ በእስረኛዋ ላይ ሲፈጽም መታየቱ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ