Teddy Afroፍርዱ ከስድስት ዓመት ወደ ሁለት ዓመት ተቀየረ

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 11 ቀን 2001 ዓ.ም. February 18, 2009)፦ ዛሬ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ሰሚ ችሎት በአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ላይ ተጥሎ የነበረውን የስድስት ዓመት እስራት አሻሽሎ ወደ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲጸና ውሳኔ ማሳለፉን የአዲስ አበባ ሪፖርተራችን ከስፍራው ዘገበ።

 

ብዛት ያለው የአርቲስቱ ዘመድ ወዳጅና አድናቂዎቹ በችሎቱ ላይ የተገኙ ሲሆን፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የፍርዱን ቅጣት ለመቀነስ የቻለበትን ምክንያት ሲያብራራ፤ ተከሻሹ አደጋውን መፈጸሙን ያረጋገጠ ቢሆንም ሟች ቀደም ብሎ በስካር በመሀል መንገድ ላይ ተኝቶ የነበረ መሆኑን በማረጋገጡና ተከሳሹ ያቀረበውን የክስ ማቅለያ ከግምት በማስገባት መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

 

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ቴዲ አፍሮ እጁ ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ ለሁለት ዓመት እስራት ቅጣት የጣለበት ሲሆን፣ እስረኛው ከባለፈው ዓመት ሚያዝያ ጀምሮ በእስር የቆየ ሲሆን፣ አመክሮ ከተሰጠው ከሦስት ወራቶች በኋላ ሊለቀቅ እንደሚችል ተገምቷል።

 

ፍርዱ ከተሻሻለ በኋላ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት በደስታ የወጡት የቴዲ አፍቃሪዎች "ሰለሜ" እና "አበባየሆሽ" የተሰኙትን የቴዲ አፍሮን ዘፈኖች እያሰሙ ሲወጡ መስተዋላቸውን ሪፖርተራችን አክሎ ዘግቧል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ