ቴዲ አፍሮ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር
ለግንቦት አራት ተቀጠረ
Ethiopia Zare (ዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን 2001 ዓ.ም. May 8, 2009)፦ ታዋቂው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከተከሰሰበት ሰው ገጭቶ ማምለጥ በተጨማሪ “ሰለሜ” በተሰኘው ክሊፕ ላይ ያለፍቃዴ ስዕሌን ተጠቅሟል በሚል ለቀረበበት ክስ ትናንት ሐሙስ ሚያዝያ 29 ቀን 2001 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር።
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰባተኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ለአንድ ዓመት ያህል ሲከታል የነበረው ቴዲ አፍሮ ፍርድ ቤቱ በዕለቱ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፤ “ውሳኔው አልደረሰለኝም” ሲል ለግንቦት አራት ቀን 2001 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ከአንድ ወር በፊት “ለውሳኔ” ብሎ መዝገቡን ቀጥሮ የነበረ ቢሆንም፤ ውሳኔውን ሠርቶ ባለማጠናቀቁ ለትናንት ቀጥሮት ነበር። ነገር ግን በዕለቱ ውሳኔው አልደረሰም በመባሉ ቴዲ አፍሮ ወደቃሊቲ እንዲመለስ ተደርጓል።



