ኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል Eng. Hailu Shawel‘ግንቦት 20 ቀን የታሪክ አጋጣሚ ምጸት ሆኖ አልፏል’ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2001 ዓ.ም. June 1, 2009)፦ ግንቦት 20 ቀን ለኢህአዲግ ሥልጣኑን የተቆጣጠረበት 18ኛ ዓመት የድል ቀን ሲሆን፣ ለእኛ ደግሞ ዲሞክራሲ የተረገጠበትና መሪያችን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ እስር የተጣለችበት አምስተኛ ወር ነው ሲሉ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

 

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የግንቦት 20 ቀን 2001 ዓ.ም. የኢህአዲግ መንግሥት 18ኛ ዓመቱን በደስታ ያከበረ መሆኑን ገልጸው፤ አንድነት ፓርቲም መሪያቸውን የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ወደ እስር መጣል ምክንያት በማድረግ የሻማ መብራት ሥነሥርዓት ከማክበራቸውም በላይ የቀድሞው ቅንጅት መሪና የመኢአድ ሊቀመንበር ኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል በሻማ መብራት ሥነሥርዓቱ ላይ ተጋብዘው መገኘታቸውንና ሁሉንም የሚያስተሳስርና የነበረውን የእርስ በርስ ችግር እስከወዲያኛው ሊያስወግድ የሚችል ታላቅ ንግግር ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

 

ኢንጂንየሩ በንግግራቸው ‘የጋራ ዓላማ ያለን የጋራ መታገያ ጊዜው አሁን ነው፣ ተቀራርበን መታገል አለብን፣ ወ/ት ብርቱካን አንድነት ፓርቲ መሪ ብቻ አይደለችም፤ የታሰረችበት ዓላማ የጋራችን ነው’ የሚል ሰፊ፣ ጠንካራና ገንቢ ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል።

 

በሜኔሶታ ሚዮ ክሊኒክ ሕክምና ላይ በነበሩ ጊዜ ከሁለት ዓመት በፊት እሳቸውን ጨምሮ ወ/ት ብርቱካንና አቶ ብሩክ በመሆን ከሁለት ዓመት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ እንዳዩዋቸው የተናገሩት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ፣ ባለፈው ሐሙስ የታሪክ አጋጣሚ ምጸት ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል።

 

ኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል በተለያዩ ጊዜያት በእንደዚህ አይነት ዝግጅት ላይ እንዲገኙ የአንድነት ፓርቲ ጥሪ ሲያደርግላቸው ቢቆይም፣ ባለባቸው የሥራ መደራረብ ምክንያት ሳይገኙ ቢቀሩም፤ በግንቦት 20 ቀን የወ/ት ብርቱካን አምስተኛ ወር እስር መታሰቢያ ላይ ተገኝተው ያደረጉት አባታዊ ንግግር የተሰብሳቢውን ስሜት ተቆጣጥሮት እንደነበር ለማወቅ ችለናል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ