የኢ/ር ኃይሉ ሻውል ቡድን ጠቅላላ ጉባዔ አካሄደ

አቶ አባይነህ ወ/ት ብርቱካን የተሸለመችውን መኪና እንደሚያስመልሱ ገለጹ

AEUP General Assembly20080622
 

Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. June 22, 2008)፦ በኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል የሚመራው ቅንጅት/መኢአድ ለጉባዔተኛውና ለጋዜጠኞች በቅንጅት ስም ጉባዔውን ጠርቶ፤ ለአዲስ አባባ መስተዳድር ለስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደግሞ በመኢአድ (በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት) ስም የስብሰባ ፈቃድ ጠይቆ፤ ዛሬ እሁድ ሰኔ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ ኢ/ር ኃይሉ ሻውልን በፕሬዝዳንትነት መረጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ሠላማዊ ትግልን ወያኔ/ኢህአዴግ አቢዩዝ አድርጎታል” አቶ ቸኮል ጌታሁን

Ginbot 7 Public meeting in Stockholm 080621 

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. June 21, 2008)፦ ዛሬ ረፋዱ ላይ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም፣ ልዩ ስሙ ኦሽታ በተሰኘ ክፍለ ከተማ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ከህዝብ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ከሰዓት በኋላ 14፡25 ሰዓት (ስምንት ሰዓት ከሃያ አምስት) ላይ ጀምሯል። በዚህ ህዝባዊ ውይይት ላይ የንቅናቄው መሥራቾች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ቸኮል ጌታሁን ተገኝተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ፓርቲ - በአዲስ መንፈስ

ልዩ ጥንቅር - በአንድነት ፓርቲ ምስረታ ላይ

የመሪዎቹን አጭር ታሪክ/Profile ይዘናል

Andenet Leaders

Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 13 ቀን 2000 ዓ.ም. June 20, 2008)፦ ሰኔ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. በኢምፔሪያል ሆቴል ጠቅላላ ጉባዔ በማድረግ አመራር ለመምረጥ በዝግጅት ላይ የነበረው አንድነት ፖርቲ በዕለቱ ባይሳካለትም ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. በተለምዶ ሪቼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት በድንኳን ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ተደርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን ከምርጫው በኋላ ያደረገችው ንግግር

UDJ leaders

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. June 18 2008)፦ በዛሬው ዕለት የተመረጡት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ከፍተኛ አመራሮች በፎቶግራፉ ላይ ከኋላ (ከግራ ወደ ቀኝ) አቶ ተመስገን ዘውዴ (ምክትል ሊቀመንበር እና የፋይናንስና የአስተዳደር)፣ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ (ምክትል ሊቀመንበር እና የህዝብ ግንኙነት)፣ አቶ አስራት ጣሴ (ዋና ፀሐፊ)፤ ከፊት (ከግራ ወደ ቀኝ) ኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራው (ምክትል ሊቀመንበር እና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ)፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ (ሊቀመንበር)፣ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም (ምክትል ሊቀመንበር እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ) ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ፓርቲ ስድሳ የላዕላይ ም/ቤት አባላት መረጠ

ከፍተኛውን ድምፅ ያገኘችው ወ/ት ብርቱካን ነች

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. June 18 2008)፦ ዛሬ የተሰበሰበው የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ስድሳ የላዕላይ ም/ቤት አባላትን የመረጠ ሲሆን፣ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ በከፍተኛ ድምፅ በአንደኛ ደረጃ ስትመረጥ ኢንጂንየር ግዛቸው በሁለተኛ ደረጃ መመረጣቸው ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ፓርቲ ለጉባዔው የስብሰባ ፈቃድ ተሰጠው

ፕ/ር ኤፍሬም ይስኃቅ ለፈቃዱ መገኘት ሚና ተጫውተዋል

ጉባዔው ነገ ረቡዕ 2፡30 ሰዓት ላይ ይጀመራል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. June 17 2008)፦ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የመሥራች ጉባዔውን ለማካሄድ የሚያስችለውን የስብሰባ ፈቃድ አገኘ። የሸምጋዮቹ ቡድን መሪ የሆኑት ፕ/ሮ ኤፍሬም ይስኃቅ ለፈቃዱ መገኘት ሚና ተጫውተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ያቆብ ኃ/ማርያም ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተው በዋስ ተለቀቁ

ከሳሻቸው አቶ አየለ ጫሚሶ ነው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. June 17 2008)፦ ዶ/ር ያቆብ ኃይለማርያም “አውራምባ ታይምስ” ከተሰኘው በሀገር ውስጥ ከሚታተም ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ተንተርሶ በአቶ አየለ ጫሚሶ በተመሰረተባቸው ክስ ትናንት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠርተው ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ በዋስ ተለቅቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአፋሮችና በኢሳዎች ግጭት አራት ሰዎች ተገደሉ

ከሟቾች አንዱ የወረዳው አስተዳዳሪ ናቸው

Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. June 15 2008)፦ ኀሙስ ዕለት "ገዳማይት" በተባለ መንደር በአፋሮችና በኢሳዎች መካከል በተቀሰቀሰ የጎሣ ግጭት አራት ሰዎች ሲሞቱ፣ ብዛት ያላቸው ለከባድና ለቀላል የመቁሰል አደጋ መዳረጋቸውን ከኢትዮጵያ የደረሰን ሪፖርት ያስረዳል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት ፓርቲ የመስራች ጉባዔው አዋዋልና መጪው ሁኔታ (ልዩ ጥንክር)

Andenet General Assembly 20080614

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. June 14, 2008)፦ በዛሬው ዕለት ሁለት ጊዜ የኢህአዴግ ፖሊሶች አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊያደርገው አቅዶት የነበረውን የመሥራች ጉባዔውን ለማጨናገፍ ያደረጉት ሙከራ የተሳካላቸው ቢሆንም፤ ጉባዔውን እስከመጨረሻው ሊያስቀሩት እንደማይችሉ ከአዲስ አበባ ያሰባሰብናቸው መረጃዎች ጠቁመዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...