በስዊዘርላን ኒዮን ከተማ የሚካሄደው የኢትጵያውያን ፌስቲቫል ዛሬ ይጠናቀቃል

ያሬድ ክንፈ ከኒዮ፣ ስዊዘርላንድ (ጥቂት ፎቶግራፎች ይዘናል)

በዓሉን ካደመቁት ሕፃናት በጥቂቱ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. July 20, 2013)፦ ረቡዕ ሐምሌ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. (ጁላይ 17፣ 2013) በኒዮን የስዊዘርላንድ ከተማ የተጀመረው 11ኛው የአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ቅዳሜ ይጠናቀቃል። ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት፣ ከሰሜን አሜሪካ፣ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከተለያዩ አህጉራት የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለበዓሉ ድምቀት አስተዋጽዖ አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከዓመት ከስድስት ወር እስር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃሊቲ ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው ተፈቀደ

ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ለሚያሰሙ ምስጋና አቅርቧል

"ስላደረጋችኹልኝ እና ስለምታደርጉልኝ ኹሉ አመሰግናለሁ!" እስክንድር ነጋ

"እስክንድር ለዚህን ያህል ወራት እስር ቤት መቆየቱን ተጠራጠርኩ፤ ጥንካሬው አሁንም አብሮት አለ" ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ Jornalist Eskinder Nega

Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. June 14, 2013)፦ ላለፉት አስራ ስምንት ወራት በእስር ላይ ያለው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በዚህ ሣምንት መፈቀዱን ለመረዳት ችለናል። ዛሬ ጠዋት ቃሊቲ ሄደው ከጠየቁት ውስጥ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ አንዷ ስትሆን፤ አላግባብ ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ላሰሙና ለሚያሰሙ ሁሉ በያሉበት ምስጋናዬ ይድረሳቸው ብሏታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በዓባይ ግድብ ላይ የተደረገ ክርክር

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 23 ቀን 2005 ዓ.ም. May 31, 2013)፦ አልጀዚራ በ"ኢንሳይድ ሰቶሪ" ዝግጅቱ የዓባይን ግድብ እንዲሁም ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ.ም. የወንዙን ተፈጥሯዊ ፍሰት አቅጣጫ እንዲቀይር መደረጉን አስመልክቶ፤ ትናንት ጋዜጠኛ ዴቪድ ፎስተር አቶ በረከት ስምዖንን ከአዲስ አበባ፣ ላማ ኤል-ካታውን ከካይሮ እና ክሊዮ ፓስካልን ከሎንዶን አሟግቷቸዋል። (ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

በታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችን ለማስወገድ የታሰበ መድረክ ተዘጋጀ

በ17 ዓመቷ ራሷን ያጠፋችው ወጣት ቤተሰቦች ልምድ ያካፍላሉ!

“በእኔ ቤተሰብ የደረሰ ልብ የሚሰብር ሀዘን በሌሎች ወገኖቼ ላይ ደርሶ ማየት አልፈልግም” (የኤደን ወላጅ አባት)

‘ልጄን እንደ ንግስት ነበር ያሳደኳት፤ የዚህ ሀገር ልጅ ምኑም አይታወቅም”  የኤደን እናት ወ/ሮ በለጡ

ደራሲ ሐምራዊት ተስፋ በውይይቱ ላይ ትናገራለች!

የአማንዳ ቶድ ወላጅ እናት በውይይቱ ተካፋይ ናቸው!

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 5ቀን 2005 .. May 13, 2012)ባለፈው መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም በቫንኩቨር ካናዳ ህይወቷን ያጣችው የ17 ዓመት ታዳጊ ወጣት ኤደን ዘውዱ ቤተሰቦች በራሳቸው ቤተሰብ የደረሰ ሀዘን በሌሎች ወገኖች ላይ እንዳይደርስ ለማንቃት ተግተው እንደሚሰሩ አስታወቁ። በኖርዝ አሜሪካ ልጆችን ለማሳደግ የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካተተ መጽሐፍ የጻፉት ደራሲ ሐምራዊት ተስፋም ተጋባዥ መሆናቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሲያትል ለኢሳት 50ሺህ ዶላር ተሰበሰበ

የጋዜጠኞቹ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙና ውብሸት ታዬ ምስል 33ሺህ ዶላር በጨረታ ተወስዷል

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዚያ 14ቀን 2005 ዓ.ም. April 22, 2013)፦ ትላንት ምሽት በሲያትል ከተማ የኢሳትን ሶስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ታማኝ በየነ እና አቶ መንሱር ኑር በክብር እንግድነት የተገኙበት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት ላይ 50ሺህ የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቤንች ማጂ አማርኛ ተናጋሪዎችን ማፈናቀል ዳግም ተጀመረ

(ፍኖተ ነፃነት ቁ. 71፣ መጋቢት 29 ቀን 2005)፦ በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሜኒት ወልድያ ወረዳ በተለይም ዘንባብና አርፋጅ ቀበሌ ነዋሪዎች በካከል ከ350 በላይ የአማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ተፈናቅለው በወረዳው አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፋሽስቱ ግራዚያኒን ሐውልት መሠራት ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ በአ.አ. ታሰሩ

”ይህ የጤንነት አይመስለኝም!” ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም Dr Yakob HailemariamEthiopia Zare (እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. March 17, 2013)፦ የፋሽስቱን ግራዚያኒ ሐውልት በጣሊያን ሀገር በመሠራት ላይ መሆኑን በመቃወም በአዲስ አበባ ሰልፍ ለማድረግ የወጡ ከ35 በላይ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ። ከእነዚህም ውስጥ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ይልቃል ጌትነት ጨምሮ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አመራር አባላት በዛሬው ዕለት ታስረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ከእኔ ልጅ ጋር ሐረር ከተማ ውስጥ አራት ሰው በፓሊስ ነዳጅ እየተደፋበት በእሳት ተቃጥሎ ሞቷል"

ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ W/o Ethiopia Yelemaወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ (ከሐረር የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸው የተባረሩ አዛውንት)

ፍኖተ ነፃነት (መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም.)፦ "ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሐረር ተባረርኩ" ሲሉ አንዲት የ67 አመት ባልቴት በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"የህወሓት/ኢህአዴግ የውስጥ ፍጥጫ፣ ዴሞክራሲን አይወልድም" ሸንጎ

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2005 ዓ.ም. March 6, 2013)፦ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች (ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴን) አባላት ጅርጅታቸው ለረጅም ጊዜ ከተዘፈቁበት አረንቋ ውስጥ በማውጣት የሀገራችንን ክብርና የህዝባችንን መብት ያረጋገጠ መሠረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ይታገሉ ዘንድ ሸንጎ መጠየቁን ለኢትዮጵያ ዛሬ በላከው መግለጫ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ