በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

ዳዊት ፋንታ
ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. ፍራንክፈርት በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ዳዊት ፋንታ
ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. ፍራንክፈርት በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare(እሁድ የካቲት 17 ቀን 2005 ዓ.ም. February 23, 2013)፦ በስዊድን የሚገኘው የኢትዮጵያ ስደተኞች ማኅበር የኢትዮጵያን ጉዳይ ከሚከታተሉ የኢሚግሬሽን ተወካዮች ጋር ፌብሪዋሪ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ውይይት አደረገ። ይህንኑም ጉዳይ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ እስር ቤት ከርመው የተፈቱት ጋዜጠኞች ማርቲን ሼቢ እና ዮሃን ፐርሾን ለኢሚግሬሽን ባለስልጣናት እንዳስረዱ አቶ ፋንታሁን ገልጸዋል።
Ethiopia Zare (ሐሙስ የካቲት 7 ቀን 2005 ዓ.ም. February 14, 2013)፦ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በተከታታይ ያሳየውን ”ጅሃዳዊ ሐረካት” የተሰኘ ፊልም አስመልክቶ፤ ሰላሳ ሦስቱ ፔቲሽን ፈራሚዎች ባወጡት መግለጫ ”ለዘመናት በፍቅርና መከባበር የኖረን ህዝብ በደረቅ ፕሮፓጋንዳ መነጣጠልና መከፋፈልም ሆነ የመብት ጥያቄውን ማዳፈን አይቻልም!” በማለት በፊልሙ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሔለን ዘውዱ
የኢሳት ኖርዌይ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዕሑድ የካቲት 3 ቀን 2005 ዓ.ም. (ፌብሩዋሪ 10 ቀን 2013 እ.ኤ.አ.) በዋና ከተማዋ በኦስሎ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ዳዊት ፋንታ
የኢትዮጵያውያን የፖለቲካና ሲቪክ ማህበር አባላት አንድነት ድርጅት በፌብሯሪ 09, 2013 ዓ.ም. ያዘጋጀው ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በታሪካዊቷ የኑረንበርግ ከተማ ተካሄደ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
የገንዘቡ መጠን በስዊድን ከክብረወሰን ተመዝግቧል
ሙስሊሙና ክርስቲያኑ አንድነቱን ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳይቷል
Ethiopia Zare(ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2005 ዓ.ም. February 11, 2013) ፦ ቅዳሜ የካቲት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም በተካሄደው የኢሳት (የኢትዮጵያ ሳተላይ ቴሌቭዥን) የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 136 ሺህ የስዊድን ክሮነር የተሰበሰበ ሲሆን፤ በዚህ ዝግጅት ላይ ሙስሊም ኢትዮጵያውን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተሳትፎ ያደረጉበት መሆኑ ታውቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...(ፍኖተ ነፃነት ጥር 27 ቀን 2005 ዓ.ም.) 33ቱ ፓርቲዎች “ኢህአዴግ ስለ አካባቢ ምርጫ የሰጠው መግለጫ የጥያቄዎቻችንን ትክክለኛነትና አግላይ አቋሙን ያረጋገጠበት ነው” በሚል ርዕስ መግለጫ አወጡ። ኢህአዴግን አቋሙን እንዲያስተካክልም አስጠነቅቀዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ጨዋታውን በሞባይሎ ወይንም በኮምፒዩተር መመልከት ይችላሉ
Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 20 ቀን 2005 ዓ.ም. January 28, 2013)፦ ነገ ማክሰኞ ጥር 21 ቀን 2005 ዓ.ም. (ጃንዋሪ 29 ቀን 2013 እ.ኤ.አ.) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከናይጄሪያ ጋር በደቡብ አፍሪካ የሚያሂደውን ጨዋታ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ በቀጥታ የሚያስተላልፍ መሆኑን በደስታ ይገልጻል። በሥራ፣ በመንገድ፣ ወይም የቴሌቭዥን ቻናል የሌላችሁ በሞባይላችሁ ወይንም በኮምፒዩተራችሁ በመጠቀም የቀጥታ ስርጭቱን ትመለከቱ ዘንድ ተጋብዛችኋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
የፕ/ት ኢሣያስ አፈወርቂ ሴት ልጅም ታግዳለች
በአገዛዙ የተማረሩ ወታደሮች የቴሌቭዥን ጣቢያውን ተቆጣጥረውት ነበር
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 14 ቀን 2005 ዓ.ም. January 22, 2013)፦ ከሁለት መቶ በላይ የሆኑ የኤርትራ መንግስት ወታደሮች መንግስታቸውን ተቃውመው በትናንትናው ዕለት ሰኞ ጀንዋሪ 21/2013 ዓ.ም. የማስታወቂያ ሚንስቴሩን መ/ቤት ከበው በቁጥጥር ስር አውለዋል። የፖለቲካ ተሀድሶ እንዲደረግና የህሊና እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ ሀሳብ እንዳላቸውም አስታውቀዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአሜሪካ ካውንስል ጄኔራል የሆኑት ካውንስሌት አን ካላጋን መርቀውታል
![]() |
| የአሜሪካ ካውንስል ጄኔራል አን ካላጋን እና ሰአሊ ያሬድ ንጉሱ |
Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 13 ቀን 2005 ዓ.ም. January 21, 2012)፦ ኢትዮጵያዊው ሰአሊ ያሬድ ንጉሱ የመጀመሪያውን ጥቁር አሜሪካዊ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ፖርትሬት ለሁለተኛ ጊዜ ቃለ መሀላ ከፈጸሙበት ከዛሬ እለት ጀምሮ በቫንኩቨር ካናዳ በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ለሶስት ሳምንታት ለእይታ መቅረቡ ታወቀ። በቫንኩቨር ካናዳ የአሜሪካ ካውንስል ጄኔራል የሆኑት ወ/ት አን ካላጋን በምረቃው ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...