የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አበረ አዳሙ አረፉ

አበረ አዳሙ

ሕይወታቸው ያለፈው በሕክምና ተቋም ውስጥ መኾኑ ተነገረ

ኢዛ (ማክሰኞ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 4, 2021)፦ ከሳምንት በፊት ሚያዝያ 19 ቀን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አበረ አዳሙ ከዚህ ዓለም መለየታቸው ታወቀ። የክልሉ መንግሥት በድንገተኛ ሕመም ምክንያት የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው መቆየቱንና ሕይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአውሮፓ ሕብረትና የኢትዮጵያ ፍጥጫ

European Union Flag

ሕብረቱ ምርጫውን አልታዘብም ሲል
ኢትዮጵያ ሕብረቱ ሉዓላዊነትን የሚጋፋ ጥያቄ በማቅረቡ ትከሳለች
በምርጫው ታዛቢ ላለመላክ የተፈለገውም ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቴን የሚጋፋ አካሔድ አልቀበልም በማለቷ ነው

ኢዛ (ማክሰኞ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 4, 2021)፦ የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ የሚካሔደውን አገር አቀፍ ምርጫ 2013 ታዛቢዎቹን እንደማይልክ አስታወቀ። ውሳኔውን የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተገባ ብሎታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ ኢሜይል ሃክ ተደረገ?

PM Abiy Ahmed

ወንጀለኞች በቀድሞ ኢሜላቸው ሐሰተኛ መረጃ እያሰራጩ በመኾኑ ጥንቃቄ አድርጉ ተባለ

ኢዛ (ማክሰኞ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 4, 2021)፦ በቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግል ኢሜይል አድራሻ የተላከ በማስመሰል እየተሰራጨ ያለ መረጃ እንዳለ በመግለጽ፤ ጥንቃቄ እንዲደረግ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ ላይ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተቃውሞ ላላቸው የ48 ሰዓት ተሰጠ

ፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ

ይህ የ48 ሰዓታት ማስታወቂያ የወጣው ለመጀመሪያ ጊዜ መኾኑ ነው

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 3, 2021)፦ ሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተቃውሞ ያላቸው በ48 ሰዓት ውስጥ ማስረጃቸውን እንዲያቀርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ። ይህ የ48 ሰዓታት ማስታወቂያ የወጣው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ከ80 ዓመት በኋላ የውጭ ወረራ ሊቃጣባት ስለሚችል ኢትዮጵያውያን በአንድ እንዲቆሙ ጠየቀ

ልጅ ዳንኤል ጆቴ

“የውጭና የአገር ውስጥ ጠላቶ ቢተባበሩም ኢትዮጵያን ሊያቆስሏት ይችላሉ እንጂ፤ አያሸንፏትም” ልጅ ዳንኤል ጆቴ

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 3, 2021)፦ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ሚያዝያ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. 80ኛ ዓመት የድል በዓልን (የአርበኞች ቀን) አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የጥንታዊት ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ከሰማንያ ዓመት በፊት የገጠማት የውጭ ወረራ የሚመስል ችግር እየገጠማት በመኾኑ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ይቁሙ አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦነግ ሸኔ የሕዝብ ማመላለሻ አስቁሞ በ15 ተሳፋሪዎች ላይ የግፍ ግድያ ፈጸመ

ኦነግ ሸኔ

የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ በዚህ ጥቃት ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል

ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 1, 2021)፦ በንጹሐን ግድያ በተደጋጋሚ እየተከሰሰ የሚገኘው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሲጓዙ ከነበሩ ተሳታፊዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ 15 ሰዎችን ገድለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ክልል ከደኅንነትና ከጸጥታ ጋር የተገናኙ ቁልፍ በኾኑ ኃላፊነቶች ላይ አዳዲስ ሹመት ተሰጠ

አቶ አገኘው ተሻገር

ሹመቱን የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር ናቸው

ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 1, 2021)፦ የአማራ ክልል ከጸጥታና ደኅንነት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ አዳዲስ ተሿሚዎችን አስቀመጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በመጨረሻም ሕወሓት እና ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ተላለፈ

TPLF

ውሳኔው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው

ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 1, 2021)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው ስብሰባ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና ኦነግ ሸኔ ላይ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቦ ውሳኔ ተላለፈ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሱዳን ወታደሮች በምዕራብ ጎንደር በኩል ዛሬ ጥቃት ሰንዝረው እንደነበር ተነገረ

Sudanese soldiers

የኢትዮጵያ ጸጥታ ኃይል ምላሽ መስጠቱ ተሰምቷል

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. April 30, 2021)፦ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ ትንኮሳዋን በግልጽ እያሳየች ያለቸው ሱዳን፤ ወታደሮቸዋ ዛሬ ዓርብ ሚያዝያ 22 ቀን ማለዳ በምዕራብ ጎንደር ዞን አካባቢ ለሰዓታት የቆየ ተኩስ ከፍተው እንደነበር እና የግብርና ካምፖችን ማቃጠላቸው ተሰማ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሠማኮ በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ግጭት በጋራ ለማስቆም ጥሪ አቀረበ

MAY Day 2021

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሠራተኞች መብት እየተጣሰ መኾኑን ገልጿል

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. April 30, 2021)፦ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በአሁኑ ወቅት በተያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየታየ ያለውን ግጭት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በመተባበር እና በመመካከር ማስቆም እንደሚገባቸው አስታወቀ። የሠራተኞች መብት እና ጥቅሞች በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እየተጣሰ መኾኑንም ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ