አቶ ታደሰ ካሣ በሌላ ክስ ስምንት ዓመት እስራት ተፈረደባቸው

ታደሰ ካሣ

20 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ተወሰነ

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 21, 2020)፦ በቅርቡ ከነአቶ በረከት ስምኦን ጋር ስምራት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳ፤ በሌላ የክስ መዝገብ ተጨማሪ የስምንት ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራትና 20 ሺሕ ብር እንደተቀጡ ተገለጸ። ጉዳዩን የያዘው የባሕር ዳር ዙሪያ ፍርድ ቤት በአቶ ታደሰ ላይ ይህንን ቅጣት ያሳለፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለአገር መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች ገለጻ ተደረገ

ጄኔራል አደም መሐመድ፣ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እና ዶ/ር ኢንጂንየር ስለሺ በቀለ

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድና ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ተገኝተዋል

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 21, 2020)፦ ከሰሞኑ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግሥት፤ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. በውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂንየር ስለሺ በቀለ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለአገር መከላከያ የጦር ኃይል አመራሮች ገለጻ ማድረጋቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ የቫይረሱ ተጠቂዎች ወደ 399 ከፍ ብሏል

Total coronavirus cases in Ethiopia, May 21, 2020

እስካሁን ለ69 ሺሕ 519 ሰዎች ምርምር የተደርጓል

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 21, 2020)፦ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ለ3,747 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጐ አስር ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው አስታውቋል። ይህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 399 መድረሱን አመላክቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የበለጠ ሥጋት እየፈጠረ ነው

Total coronavirus cases in Ethiopia, 2020-05-20

የውጭ ጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተጠቃ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ሰዎች የበለጠ በቫይረሱ እየተጠቁ ነው

ኢዛ (ረቡዕ ግንቦት ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 20, 2020)፦ የኮሮና ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰቱ ከተሰማ ሁለት ወራት በላይ ቢቆጠሩም፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ችግሩ አደገኛ እየኾነ መምጣቱን እያመላከተ ነው። ዛሬ በ24 ሰዓታት ውስጥ የተደረገውን የምርመራ ውጤት ተከትሎ ከተሰጠው ሪፖርት በኋላ የጤና ሚኒስትሯ የሰጡት መግለጫም አሁን በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የወረርሽኙ ሥርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣቱን የሚያስረዳ ነው። የውጭ ጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተጠቃ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ሰዎች የበለጠ በቫይረሱ እየተጠቁ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የመቀሌውን ግድያ አወገዘ

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ

ድርጊቱ በትግራይ የሰላምና ዴሞክራሲ እጦት ማሳያ ነው ብሏል

ኢዛ (ማክሰኞ ግንቦት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 19, 2020)፦ ከሁለት ቀናት በፊት በመቀሌ ከተማ ለአንድ ወጣት ሕይወት ሕልፈትና ለሁለት ወጣቶች የምቁሰል አደጋ በትግራይ ክልል ውስጥ የሰላምና ዴሞክራሲ እጦት ማሳያ ነው ሲል፤ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ዛሬ (ማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም.) ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከባንክ በጥሬ የሚወጣ ገንዘብ ገደብ ተጣለበት

Dr. Yinager Dessie

ግለሰብ በቀን 200 ሺህ፣ ኩባንያዎች በቀን 300 ሺህ ብቻ ማውጣት ይችላሉ

ኢዛ (ማክሰኞ ግንቦት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 19, 2020)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገንዘብ አስቀማጭ ግለሰቦችና ኩባንያዎች በየዕለቱ ከባንኮች የሚያወጡትን ጥሬ ገንዘብ የሚገድብ አዲስ መመሪያ ከዛሬ ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ላይ አዋለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 36ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 36rd, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ ሠላሳ ስድስተኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከግንቦት 3 - 9 ቀን 2012 ዓ.ም.) ያሳለፍነው ሳምንት በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሕገ መንግሥት ትርጓሜን በተመለከተ የሕግ ምሁራን በግልጽ የመከሩበት መድረክ ተዘጋጅቶ ውይይት የተደረገበት ነው። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የሕገ መንግሥት አጣሪ ኮሚቴ ሰብሳቢም በሕገ መንግሥቱን ትርጓሜ ላይ የተደረገ የመጀመሪያው መድረክ ስለመኾኑ ሳያመለክቱ አላለፉም። በዚህ መድረክ ላይ የሕግ ምሁራን የተለያዩ አስተያየቶችነ የሰጡበት ሲሆን፤ ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም እንዲሰጥ መወሰኑ አግባብ እና የተሻለ አማራጭ ስለመኾኑ ብዙዎች የጠቆሙበት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ከአስቸኳይ አዋጁ ጋር በተያያዘ በፖሊስ ሁለተኛ ሰው ተገደለ

መቀሌ

የትግራይ መገናኛ ብዙኀን እስካሁን ስለጉዳዩ አልዘገቡም

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 18, 2020)፦ በትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌዎችን ለማስከበር በሚል በተፈጠረ ግጭት በመቀሌ አንድ ሰው ሲሞት፤ ሁለት መቁሰላቸው ተረጋገጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በተቀዛቀዘ ኢኮኖሚ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ አሥር በመቶ ጨምሯል

Chat

አበባ፣ ጫት፣ አትክልትና ፍራፍሬ ጉልህ ድርሻ ነበራቸው

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 18, 2020)፦ የዓለም ኢኮኖሚ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ በተመታበት በዚህ ወቅት፤ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ አፈፃፀም ከቀደሙት ወቅቶች የተሻለ በመኾን በዘጠኝ ወራት 2.09 (ሁለት ነጥብ ዜሮ ዘጠኝ) ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተመለከተ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአንድ ቀን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 35 ሰዎች ተገኙ

Total coronavirus cases in Ethiopia, 2020-05-08

29ኙ በአዲስ አበባ የተገኙ ናቸው

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 18, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዕለታዊ ሪፖርት ይፋ መደረግ ከጀመረበት መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ወዲህ በ24 ሰዓት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን የሚያመለክት ሪፖርት ዛሬ ይፋ ኾኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ