አምስት የፌዴራሊስቱ ጥምረት አባላት ታስረዋል ተባለ

Dereje Bekele

ከገለልተኛ አካል ማረጋገጫ አልተሰጠም
በሕወሓት ይመራል የተባለው ቡድን ጽሕፈት ቤቱን አዲስ አበባ ሊያደርግ ወሰነ

ኢዛ (እሁድ ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 17, 2020)፦ በመቀሌ ከተማ ሊካሔድ በነበረው የኢትዮጵያ የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ መቀሌ ለመሔድ ሲዘጋጁ የነበሩ የጥምረቱ አመራሮች ታስረዋል ሲል የትግራይ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በእነአቶ ልደቱ የሚመራው ፓርቲ የሽግግር መንግሥት ምሥረታው የማልተወው አቋሜ ነው አለ

አብሮነት

የሽግግር መንግሥቱ የማይቋቋም መኾኑ አደጋ አለው በማለት መግለጫ አውጥቷል

ኢዛ (እሁድ ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 17, 2020)፦ ሦስት ፓርቲዎችን በአባልነት የያዘው አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ቋሚ የትግል አጀንዳችን ኾኗል በማለት ዛሬ እሁድ ግንቦት 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርጫ ቦርድ 27 ፓርቲዎችን ሰረዘ

ኢንጂንየር ይልቃል ጌትነት፣ አቶ ሸዋንግዛው ገብረሥላሴ

የ76 ፓርቲዎችንም ጉዳይ እየመረመረ ነው

ኢዛ (ዓርብ ግንቦት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 15, 2020)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲሱ የፓርቲዎች ምዝገባ ሕግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ የተደረገላቸውን ጥሪ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ አላሟሉም ያላቸውን 27 የፖለቲካ ፓርቲዎችን መሰረዙን አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ደብረጽዮን በትግራይ ክልል የተናጠል ምርጫ ይደረጋል አሉ

Dr. Debretsion GebreMichael

“ከድርጊቱ የማይቆጠብና ይህንን የሚያደርግ ከኾነ መንግሥት እርምጃ ይወስዳል” ብልጽግና

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 14, 2020)፦ በአገር አቀፍ ደረጃ ምርጫ የማይካሔድ ከኾነ፤ በትግራይ ክልል ውስጥ ምርጫን የሚያደርግ ስለመኾኑ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የገለጹ ሲሆን፤ የብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ይህ አይሞከረም እያለ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልሎች ጋር መክረዋል

PM Abiy Ahmed

አዘዋዋሪዎችን ለመቆጣጠር ሁሉን አቀፍ ስምሪት ያስፈልጋል ብለዋል

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 14, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከክልል አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት በሕገወጥ መንገድ የጦር መሣሪያን ማስገባትና መዘዋወርን ለመግታት፤ እንዲሁም አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሁሉንም ስምሪት እንደሚጠይቅ አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአዲስ አበባ ባለኮኮብ ሆቴሎች በወር 35 ሚሊዮን ዶላር እያጡ ነው

Best Western Plus Addis Ababa

ብሔራዊ ባንክ ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚሰጥ ብድር አመቻቸ

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 14, 2020)፦ በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለኮኮብ ሆቴሎች የኮሮና ወረርሽኝ በአገሪቱ መከሰቱ መገለጽ ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ በየወሩ ከ35 ሚሊዮን ዶላር በላይ (1.57 ቢሊዮን ብር) ገቢ እያጡ መኾኑን የአዲስ አበባ ሆቴሎች ማኅበር ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ጥያቄውን በአጭር ጊዜ ለመመለስ እየተሠራ ነው ተባለ

 ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ

አጣሪ ኮሚቴው በአሥር አባላት ሥራ ጀምሯል

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 14, 2020)፦ በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበውን የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ጥያቄ በአጭር ጊዜ ምላሽ እንዲያገኝ እየተሠራ መኾኑን የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢዋ አስታወቁ። በትርጓሜው ዙሪያ ከሕግ ባለሙያዎች ጋር በመኾን የሚደረገው ውይይት ለሕዝብ ይተላለፋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 35ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 35rd, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ ሠላሳ አምስተኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከሚያዝያ 26 - ግንቦት 2 ቀን 2012 ዓ.ም.) ያሳለፍነው ሳምንት በዋና አገራዊ አጀንዳነት የሚጠቀሰው የምርጫ 2012 መራዘምና ይህንኑ ተከትሎ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችና ውሳኔዎች ናቸው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀጣዩን ምርጫ ለማካሔድ ያስችላል ብሎ ሕገ መንግሥታዊ ትርጓሜ በሚሰጠው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ላይ ውሳኔ ማሳለፉም የዚሁ የሰሞነኛ አጀንዳ አካል ሲሆን፤ በዚህ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕግ ምሁራን እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች በሰፊው አስተያየት የተሰጠበትም ኾኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለመዝረፍ የተደረገ ሙከራ ከሸፈ

National Intelligence & Security Service (NISS), Ethiopia

ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል

ኢዛ (እሁድ ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 10, 2020)፦ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓትን በመጠቀም፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር (110 ሚሊዮን ዶላር) የማጭበርበርና ዘረፋ ወንጀል መክሸፉን አስታወቀ። እስካሁን አንድ ናይጄራዊ ጨምሮ ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 34ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 34rd, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ ሠላሳ አራተኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከሚያዝያ 19 - 25 ቀን 2012 ዓ.ም.)፦ ያሳለፍነው ሳምንት በአገራችን ወሳኝ የሚባሉ አገራዊ አጀንዳዎች ለምክክር የቀረቡበት ነበር ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተደራራቢ ችግሮች ከፊቷ የተደቀኑባት እንደመኾኑ መጠን፤ እነዚህን ችግሮች እከሌ ከከሌ ሳይባል በጋራ መምከርና ይህንን ችግር እንዴት እንሻገር ብሎ አጀንዳ ቀርፆ መነጋገርም ግድ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ