”ወራዳ ሌባ ነው፣ ... ቆሻሻ ...፣ የአድኀርያን፣ የሻገተ አመለካከት ይዞ ...” ጠ/ሚ መለስ በፓርላማ
ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሚያዝያ 5 ቀን 2002 ዓ.ም. ለፓርላማው ሪፖርት አቅርበዋል። በዕለቱ ጠ/ሚንስትሩ ”... ወራዳ ፍጥረት ነው። አሁንም ልድገመው - 'አቶ ልደቱ አዲስ ኃይማኖት አምጥተዋል' ብሎ የቀሰቀሰ የእኛ ሰው ካለ፤ ያ ሰው የእኛ ሰው አይደለም፤ ያ ሰው ወራዳ ሌባ ነው። ልድገመው ወራዳ ሌባ ነው። ይሄ ከኢህአዲግ ጋር በምንም መልኩ ሊገናኝ የማይችል የወራዶች አመለካከት ነው። የኋላቀሮች የአድኀርያን አመለካከት ነው። እንዲያ አይነት ቆሻሻ ይዞ ኢህአዲግ ጋር መጠጋት አይገባውም ማንም ሰው ቢሆን። የሻገተ አመለካከት ይዞ ኢህአዲግ ጋር መጠጋት የለበትም። ...” ሲሉ ተደምጠዋል።
በዕለቱ ጠ/ሚንስትሩ ፀያፍ ቃላትን ከመጠቀማቸው በተጨማሪ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የፓርላማ ተወካዮች ጠ/ሚንስትሩ በጥያቄ አፈጥጠዋቸዋል። ጠ/ሚ መለስ ፀያፍ ቃላትን እንዳሻቸው ሲጠቀሙ፤ ሥርዓት ባለው መንገድ የሚናገሩትን ተቃዋሚዎች ግን አፈጉባዔው እንዳይናገሩ ሲያግዷቸው ይህ ቪዲዮ ያሳያል። ለአንባብያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የ6 ደቂቃ ከ26 ሰከንዱን ቪዲዮ ይመለከቱ ዘንድ እንጋብዛለን።



