ሠላም (ቦጋለ ዳኜ)
ሠላም
ቦጋለ ዳኜ - ከካሊፎርንያ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
“ዘብ! ተጠ ... ንቀቅ!
ብረ ... ት አውጣ!
ለግርማዊ ጃንሆይ
በብረት ሠላ ... ም በል!
ብረ ... ት አውርድ!
አሳ ... ርፍ!”
በብረት ሠላም መስጠት፤
በብረት ሠላም መንሳት፤
ለሠላም ብረት ማንጋጋት
ለመዓትም ብረት ማንጋጋት
ሆነና ነገር እንዳደረጉት።
እባክህ አምላከ-ሠላም
አምላከ- ሠላም ወምህረት
አንተ ሠላም በል
አይደለም ሠላም በብረት
አንሻም ሠላም በብረት
የምንሻው በምድር ነው ...
ሠላም በምድር
ሠላም በመላ ዓለም
ሠላም-ጠሎችን
አንተ አሳርፍ።
እባክህ ፍጠር አዲስ ዓለም
ብረት የሌለባት ዓለም።
ቦጋለ ዳኜ - ከካሊፎርንያ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.